በኦክቶበር 2022 በካውንስልሜምበር ብርያን ነዶው ተዘጋጀቶ የቀረእበው የሎካል ሬሲደንትስ ቮቲንግ ራይትስ አክት የተባለውና የአሜሪካ ዜግነት የሌላቸው የዲሲ ነዋሪዎች በአካባቢያዊ ምርጫዎች በመምረጥ መመረጥ መሳተፍ እንዲችሉ የሚያስችላቸው ህግ በብርያን ነዶው ተረቅቆ በካውንስሉ ጸድቆ ነበር።
ባሳለፍነው ሰሞን ታዲያ በዋሺንግተን ዲሲ የመጀመሪያው የአሜሪካ ዜግነት የሌለው ሰው ለመንግስት ቢሮ ተመርጧል። ይህም ሰው ኢትዮጵያዊው አቤል አመነ ነው። አቤል በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ካሉትና አድቫዘሪ ኔይበርሁድ ኮሚሽን ውስጥ በኮሚሽነርነት ለማገልገል በዋርድ 4 ካውንስልሜምበር ጄኒስ ቃለመኃላ ፈጽሞ ኮሚሽነርነቱን ተቀብሏል። አቤል ከኢትዮጲክ ባልደረባ ከሔኖክ ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ።
ሁሌም ትኩስ መረጃዎቻችንን ለማግኘት በፌስቡክ ይከተሉን