05/18/2024

የብሄራዊ አየር ንብረት ጣቢያ ነገ በዲሲና አካባቢው ጎርፍ ሊኖር እንደሚችል በዋናነትም ለፖቶማክ ወንዝ አቅራቢያ ባሉና ረባዳማ በሆኑ አካባቢዎች የበረታ እንደሚሆን አሳውቋል፡፡ ነዋሪዎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል፡፡ ይህም ስጋት ከነገ ማክሰኞ 01/09/2024 ምሽት 10pm  እስከ ረቡዕ 01/10/2024 ጠዋት 10am ነው፡፡

በዚህ ወቅትም ታዲያ ከመሬት ወለል በላይ ከአንድ እስከ ሁለት ጫማ የሚደርስ የውኃ መጥለቅለቅ በዝቅተኛ/ረባዳ ቦታዎች ላይ ሊስተዋል እንደሚችልና በእለቱ የሚዘንበው ዝናብ ደሞ ለጎርፉ መባባስ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ጎርፍ በዋናነት የፖቶማክ ወንዝን ተንተርሰው ባሉ የዲሲ አካባቢዎች ላይ እንደሚስተዋል ተጠቅሷል፡፡

 የጥንቃቄ/የዝግጅት እርምጃዎች፡ ጉዞ የሚያስፈልግ ከሆነ፣ አንዳንድ መንገዶች ሊዘጉ ስለሚችሉ ተጨማሪ ጊዜ ይስጡ። የተዘጋ መንገድ አቋርጠው ለመሄድ አይሞክሩ፡፡ ጥልቀቱ በማይታወቅ የተጠራቀመ ውሀ ላይ አይንዱ፡፡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራስዎንና በጎርፍ ሊበላሹ የሚችሉ ንብረቶችዎን ከጥፋት ያድኑ፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት