12/12/2024
2

ነገ ይኖርል ተብሎ በሚጠበቀው ዝናብና ጎርፍ ምክንያት የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ይዘጋሉ ተብሏል። በተጨማሪም ከሰዓት የሚኖረውንና እስከ 40ማይል በሰዓት የሚምዘገዘግ ንፋስ ዛፎችንና የኤሌክትሪክና ስልክ እንጨቶችን ሊደረምስ እንደሚችል፤ ይህን ተከትሎም የአገልግሎት መቆራረጦች ሊኖር እንደሚችል ተጠቁሟል


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክናበቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


እስካሁን (01/08/2024 – 11፡13pm) ባለው መረጃ በሜሪላንድ የአን አረንደል ካውንቲ፤ የሴንት ሜሪ ካውንቲና የኪንግ ጆርጅ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ከወትሮ በ2 ሰዓት ቀድመው ይዘጋሉ።

በተያያዥ የፋኪር ካውንቲ ህዝብ ትምህርት ቤቶች እኩለቀን ላይ ይዘጋሉ። ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደሞ 11am ላይ ይዘጋሉ።

በቨርጂንያ የስፖልትስቬንያ፤ የከልፔፐር ካውንቲ የህዝብ ትምህርትቤቶና የኦሬንጅ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ዝግ ይሆናሉ። የስታፎርድ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ደሞ በ2 ሰዓት ቀደም ብለው ይዘጋሉ።

UPDATE: 11:53PM – የሆዋርድ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ነገ ማክሰኞ 01/09 በ3 ሰዓት ቀድመው እንደሚዘጉ አስታውቀዋል።

UPDATE: 01/09/24 – 12:06AM ; የፍሬድሪክስበርግ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የፕሪስኩል፤ ዎከር ግራንድ ሚድል ስኩልና ጄምስ ሞንሮ ሀይስኩል እኩለ ቀን ላይ ይዘጋሉ። የሂው መርሰር ኤለመንታሪ፤ እና የላፋዬት ኤለምንታሪ 12፡45 ላይ ይዘጋሉ።

UPDATE:- 1/9 – 7:40am- የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች በ2 ሰዓት ቀድመው ይዘጋሉ::

UPDATE:- 1/9 – 9:00am- የሞንጎምሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች በ2ሰዓት ተኩል ቀድመው ይዘጋሉ:: 1:20pm ላይ ማለት ነው

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት