Image Credit: ussoccer.com

Image Credit: ussoccer.com

ናኦሚ ባሳለፍነው አመት በሴቶች የአለም ዋንጫ ላይ አሜሪካን ወክላ በተከላካይነት ባሳየችው ድንቅ ችሎታ እንዲሁም አመቱን ሙሉ ለክለቧ ለ ሳን ዲዬጎ ዌቭ ባበረከተችው ድንቅ አስተዋጾ የአመቷ ምርጥ የሴቶች የእግር ኳስ ተጫዋች ተብላ ለመመረጥ በቅታለ፡፡ ናኦሚ ይህን ክብር የተቀናጀች በ39 ዓመት የአሜሪካ የሴቶች እግር ኳስ ሽልማት ታሪክ የመጀመሪያዋ ተከላካይ ተጫዋች ነች፡፡


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ናኦሚ በ2020 የአሜሪካ ምርጥ ታዳጊ የእግር ኳስ ተጫዋች በመባል ተሸልማ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ለዚህ ክብር መብቃቷን አስመልክታ ናኦሚ ለዚህ ክብር የበቃች ብቸኛዋ ተከላካይ በመሆኗ እንዲሁም ሁለተኛዋ ጥቁር በመሆኗ ክብር እንደሚሰማትና ይህ ሽልማት 2023 የተከላካዮችና የግብ ጠባቂዎችን ከባድ አስተዋጾ የታየበት ዓመት በመሆኑ ለተከላካዮችና በረኞች ጓደኞቿ ታሪካዊ አመት እንድሆነ ተናግራለች፡፡

ደጋፊዎቿ ይህንን ሊንክ በመጫን የናኦሚን ማልያ በመግዛት መልበስ እንደሚችሉና ድጋፋቸውን ማሳየት እንደሚችሉ ዩኤስ ሶከር አስታውቋል፡፡

ለጥቆማው ራስ አስራትን እናመሰግናለን፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.