12/12/2024
Image Credit: Capital City Public Charter School

Image Credit: Capital City Public Charter School

የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት ዩዝ ፕሮግራም በዘንድሮው የታዳጊዎች ፕሮግራሙ እንዲሳተፉ ሁለት የዲሲ ታዳጊዎችን መርጧል፡፡ በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የተመረጡትም የከፍተኛ ሁለተኛ ትምህርት ተቋማት ሲኒየር የሆኑት ኢዚኪዬል ሉ እና ብሩክታዊት ተስፋዬ ናቸው፡፡


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


በዚህም ፕሮግራም ላይ ከዲሲ የሴኔት ተወካይ ኤሊኖር ሆምስ ኖርተንጋ በመሆን በ62ኛው አመታዊ የዋሽንግተን የዩኤስ ታዳጊዎች የሴኔት ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ኢዚኪዬልና ብሩክታዊት ከበርካታ የዲሲ ተማሪዎችጋ ተወዳድረው በማሸነፍ ለዚህ እድል እንደበቁና በፕሮግራሙ ላይ ከሌሎች ስቴቶች ከመጡ 104 የተማሪ ተወካዮችጋ በመሆን ፕሮግራሙን ይሳተፋሉ፡፡ በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የተመረጡ በሙሉ የ10000$ ስኮላርሺፕ ድጋፍ እንደሚያገኙም ተነግሯል፡፡

  • Image Credit; Capital Charter Public School FB Page

ብሩክታዊት ተስፋዬ የካፒታል ሲቲ የዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ተማሪ ስትሆን በተማሪዎች የመንግስት ማህበር በፕሬዘደንትነት በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ብሩክታዊት ፒፕል ኦፍ ኢትዮጵያ የተባለ ፕሮጀክት ከጓደኞቿጋ በመጀመር የትምህርትና ሌሎችም መሰረታዊ ፍላጎት ችግር ላለባቸው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች የገንዘብ፤ የሀሳብና ቁሳቁስ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡

ይህ ፕሮግራም በሚደረግበት ሳምንት እነዚህ ታዳጊዎች በወሳኝ የመንግስት ምክክሮችና ስብሰባዎች ላይ ከሴናተሮችጋ፤ ከፕሬዘደንቱጋ፤ ከሱፕሪም ኮርት እንዲሁም በየደረጃ ካሉ የካቢኔ አባላትጋ በቅርበት ይሳተፋሉ፡፡

ብሩክታዊት በ2017 በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ለዕድሜዋ በጣም ግሩም የሆነ ንግግር በማድረግ ሚሼል ኦባማን ወደ መድረክ ጋብዛ ነበር፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት