12/12/2024
የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የላላ ብሎን አላቸው ተባለ (11)

የዋሽንግተን ዲሲ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የቧንቧ ውኃ ማስጠንቀቂያውን ከዛሬ ዕሁድ ጃንዋሪ 21 ንጋት 5ሰዓት ጀምሮ አንስቶታል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ ባደረገው ምርመራ የቧንባ ውኃውን ለማንኛውም አይነት አገልግሎት ለመጠቀም የሚያበቃው ደረጃ ላይ እንዳለና ነዋሪዎች ያለስጋት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


በማስጠንቀቂያው ተካተው በነበሩ የዲሲ ሰፈሮች የሚኖሩ ደንበኞች የቧንቧ ውኃ መጠቀም ከመጀመራቸው በፊት የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ቀዝቃዛ ውኃውን ከፍተው ለ10 ደቂቃ ያህል እንዲፈስ ያድርጉ
በመኖሪያዎት ያለው ውኃ የታወቀ የሊድ ንጥረ ነገር ካለው የ NSF/ANSI Standard 53 የተባሉና የሊድ-ሰርቲፋይድ የሆኑ ማጣሪያዎችን ይጠቀሙ
ባልተፈላ የቧንቧ ውኃ የተሰሩ ምግቦች፤ መጠጦችና በረዶዎችን አውጥተው ይጣሉ።
በቤትዎ ያሉ የውኃ ማጣሪያዎችን ባለፉት ሁለት ቀናት ተጠቅመው ከነበረ የነዚህን እቃዎች ማኑዋል በማንበብ ያጽዷቸው።

በተጨማሪም ይህን መረጃ አይደርሳቸውም ብላችሁ ለ\ምታስቧቸው ሰዎች አጋሯቸው ሲል የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫው አሳውቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት