05/18/2024

 ሎርድ ደንሞር የኢትዮጵያ ክፍለ ጦር በሚል ስያሜ ያቋቋመውና በዘመኑ በጥቁሮች ብቻ የተዋቀረው የእንግሊዝ ቀኝ ገዢዎች ክፍለጦር ከአሜሪካ ነጻነት አንድ አመት ቀድሞ በ1775 ነበር የተመሰረተው፡፡ ይህ ክፍለጦር አሁን በገቨርነር ግሌን ያንኪን በምትደዳደረው የቨርጂኛ ግዛት የወቅቱ አስተዳዳሪ ሆኖ ያገልግል በነበረው የመጨረሻው የእንግሊዝ ባለስልጣን ኧርል ኦፍ ደንሞር ከአሳዳሪዋቻቸው ያመለጡ ባርያዎችን በመሰብሰብ የኢትዮጵያ ክፍለጦርን አቋቋመ፡፡ ሎርድ ደንሞር ጦሩን ለሚቀላቀሉ ጥቁሮች ነጻነትን እንደሚሰጥ ቃል መግባቱን ተከትሎ በርካቶች ተቀላቀሉት፡፡


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ይህ ክፍለጦር ለእንግሊዝ የተሰለፈ የመጀመሪያው የጥቁሮች ክፍለጦር ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ በወርኃ ዲሴምበር 1775 ይህ ክፍለጦር 300 ጥቁር ወታደሮች ነበሩት፡፡ ከነዚህም ውስት ከሁሉም ስሙ ገዝፎ የሚወጣውና ቲተስ የተባለው ባሪያ ይገኝበታል፡፡ ቲተስ ከማንማውዝ ካውንቲ ኒው ጀርሲ አምልጦ ነው ይህን ጦር የተቀላቀለው፡፡ ቲተስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስሙን ወደ ታይ የቀየረ ሲሆን የጦር ሜዳ ማዕረግ በማግኘቱም ኮሎኔል ታይ ይባል ነበር፡፡

ፎቶ ከ፡ smithsonian african american museum

ፎቶ፡ smithsonian african american museum

ኮሎኔል ታይና ጓዶቹ ታዲያ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ከልባቸው በሰሜን አሜሪካ የነበሩ ጥቁሮችን ነጻነት ለማረጋገጥ ይዋጉ እንደነበር በታሪክ ተቀምጧል፡፡ ይህ Yእኢትዮጲያ ክፍለ ጦር ታዲያ ከ1775 የአሜሪካ አማጽያን አሸንፈው ነጻ እስከወጡበት 1776 ድረስ ውጊያ ላይ ነበር፡፡ በዋናነትም ይህ ክፍለ ጦር አሁን በቨርጂንያ ቢች አቅራቢያ በተደረገውና  ባትል ኦፍ ኬምፕስ ላንዲንግ የተሳተፈ ሲሆን የአማጺዎቹን መሪዎች በመማረክ ደምስሷቸዋል፡፡ ከተማረኩት ኮሎኔሎች አንዱ የተማረከው በገዛ ባሪያው እንደነበር ታሪክ ይጠቁማል፡፡

በዘመኑ ጥቁሮችን የመሳሪያ ተኩስ አለማምዶ ወደጦር ሜዳ መውሰዳቸው ትልቅ አብዮታዊ እርምጃ ነበር፡፡ በሰሜን አሜሪካ ለነበሩ በርካታ ጥቁሮችም የተስፋ ምልክታቸው እንደነበር

የኢትዮጵያ ክፍለጦር ወታደሮች በወቅቱ የሚያደርጉት ዩኒፎርም ላይ ነጻነት ለባሮች (“Liberty to Slaves”) የሚል ጽሁፍ ነበረው፡፡ በ1776 ይህ ክፍለጦር በኒውዮርክ ስታተን አይላንድ ተበትኗል፡፡

ምንጭ ዊኪፒዲያ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት