የኩዌከር አጃ አምራች በርካታ የግራኖላ ባርና ሲሪያል ምርቶቼ ሳልሞኔላ በተባለ በሽታ አማጭ ባክቴሪያ ተጠቅተው የመሆን እድል ስላላቸው ደንበኞቹ የገዟቸውን ምርቶች እንዲመልሱ አስጠነቀቀ። ሳልሞኔላ እጅግ አደገኛ የሆነ በተለይም በህጻናትና አዛውንቶች እንዲሁ የሰውነታቸው በሽታን የመከላከል አቅም የተዳከሙ ሰዎች ላይ እስከ ሞት የሚደርስ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ባክቴሪያ ነው።
ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::
በበሽታው የተያዙ ሰዎች በአብዛኛው እንደ ትኩሳት፤ ተቅማጥ (አልፎ አልፎ ደም የቀላቀለ)፤ ማቅለሽለሽ፤ ትውከትና የሆድ ቁርጠት ምልክቶችን ሊያሳዩ እንደሚችሉ የፌደራል መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። እነዚህ የይመለሱ አዋጅ የወጣባቸው የኩዌከር አጃ ምርቶች በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች በሽያጭ ላይ ውለዋል። በቤታቸው ምርቶቹ ያሏቸው ሰዎችም የኩዌከር አጃ የሸማቾች ግንኙነት ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጧት 10 እስከ 5፡30 በ 800-492-9322 በመደወል ወይንም በድረገጻቸው በመሄድ ገንዘብዎን ማስመለስ ወይንም ተጨማሪ መረጀ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::
ይህ የይመለሱልኝ ጥሪ የወጣባቸው ምርቶች የሚከተሉት ናቸው።
Quaker Granola Bars
Quaker Cereal
Cap’n Crunch Treat Bars, Cereal, Instant Oatmeals
Gamesa Marias Cereal
Gatorade Protein Peanut Butter Chocolate Bars
Munchies Mix Munch Mix
Snack Boxes
የይመለሱልኝ ጥሪው የሚከተሉትን ምርቶች አያካትትም።
Quaker Oats
Quaker Instant Oats
Quaker Grits
Quaker Oat Bran
Quaker Oat Flour
Quaker Rice Snacks