05/04/2024

ዛሬ አርብ 02/16 ለቅዳሜ ለሊት በዲሲና አካባቢው ከ3-እስከ 5 ኢንች በረዶ ሊጥል ይችላል ሲል የብሄራዊ አየርንብረት አገልግሎት አስታውቋል። ይህን ተከትሎም የአካባቢ የመንግስት ቢሮዎች ለነዋሪዎቻቸው የተጠንቀቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ይህ የብሄራዊ አየር ንብረት ማስጠንቀቂያ በተለይም የላውደን ካውንቲን፤ የቦልቲሞር፤ የሞንጎምሪና የሆዋርድ ካውንቲዎችን በከባዱ እንደሚያጠቃ አስታውቋል። በተጨማሪም ሰሜናዊ ፋኪር ካውንቲ፤ የፕሪንስ ዊልያም ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎችን እንዲሁ በከባዱ እንደሚያጠቃና በእነዚህ አካባቢዎች ጉዞ ማድረግ አዳጋች የመሆን እድል እንዳለው አክሎ አብራርቷል።

እነዚህ አካባቢዎች ከእኩለለሊት ጀምሮ እንስከ ንጋት 5ሰዓት ድረስ በጥቅሉ በሰዓት ከ1-2 ኢንች የበረዶ ቁልል እንደሚያጋጥማቸው ተነግሯል። ዲሲዎች ከ2 እስከ 4 ኢንች በረዶ ሊኖራቸው እንደሚችልና ደቡባዊ የሜሪላንድ አካባቢዎች እስከ 2 ኢንች በረዶ ቁልል ሊኖር እንደሚችል ተጨምሮ ተገልጿል።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት