12/12/2024
በስተርሊንግ የመኖሪያ ቤት ፍንዳታ አንድ ሰው ለህልፈት ተዳረገ - 13 ሆስፒታል ገብተዋል

ትላንት ማምሻውን በሰሜናዊ ቨርጂንያ ስተርሊንግ በሚገኝ የመኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ ፍንዳታ የአንድ የእሳት አደጋ ተከላክይን ህይወት ቀጥፏል። በተጨማሪም 13 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል እንደሚገኙ የላውደን ካውንቲ እሳትና ድንገተኛ ተከላክይ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። በሰዓቱ ፍንዳታው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የታኮማ ወንዝን ተሻግረው ባሉ የሞንጎምሪ ካውንቲ አካባቢዎችም ተሰምቶ እንደነበር ነዋሪውች አሳውቀው ነበር።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


የላውደን ካውንቲ ዛሬ እንዳሳወቀው በአደጋው ለህልፈት የተዳረገው ባልደረባቸው የሆነውና ከ2016 ጀምሮ በላውደን ካውንቲ የእሳት አደጋ መከላከያ ውስጥ ያገለግል የነበረው የ45 አመቱ ትሬቨር ብራውን እንደሆነ ተነግሯል።

አደጋ ደርሶባቸው በሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ካሉት 13 ሰዎች 11ዱ የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች እንደሆኑ ተጨምሮ ተገልጿል።

የፎክስ 5 ዲሲ ጋዜጠኛ የሆነው ኬኔዝ መተን በኤክስ አካውንቱ እንዳጋራው አደጋው የደረሰበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ፈርሷል።

የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች አስቀድመው በመኖርያ ቤት ውስጥ የተገኙት የጋዝ ሽታ አለ መባሉን ተከትሎ ነበር:: የፍንዳታው ትክክለኛ መንስዔ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል::

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት