05/04/2024

የአይ አር ኤስ የበጎ ፈቃደኛ ታክስ አዘጋጆች (Volunteer Income Tax Assistance (VITA)ና Tax Counseling for the Elderly (TCE)) ከ60 አመት በላይ በመላው አሜሪካ ለሚገኙና የፕሮግራም መመዘኛውን ለሚያሟሉ ታክስ ከፋዮች የነጻ ታክስ አገልግሎት ሲያቀርብ ቆይቷል።



ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ይህ የበጎ ፈቃደኞች ማህበር ታዲያ ዘንድሮም በየካውንቲውና ዲስትሪክቱ ይህንኑ ነፃ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግና መመዘኛውን ለሚያሟሉ ታክስ ከፋዮች የ2023 ታክሳቸውን ፋይል እንዲያደርጉ ለማገዝ በጎ ፈቃደኞችን አሰባስቦ ስራ እንደጀመረ ተነግሯል። 
በዚህ ፕሮግራም ለመጠቀም የተፈቀደላቸው

  • አመታዊ ገቢያቸው 64,000$ ና ከዚያ በታች የሆኑ
  • የአካል ጉዳት ያለባቸውና
  • በእንግሊዝኛ ቋንቋ መግባባት የሚቸገሩ ታክስ ከፋዮች ሲሆኑ በተጨማሪም እድሜያቸው 60 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ለአዛውንቶች በተዘጋጀ ተመሳሳይ ፕሮግራም መሳተፍ እንደሚችሉ ትገልጿል።

ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


በዚህ ፕሮግራም በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ታክስ ከፋዮች በሙሉ የአይ አር ኤስ ሙሉ ፍቃድ ያላቸውና መመዘኛውን ወስደው ያለፉ ባለሞያዎች ሲሆኑ አይ አር ኤስም ፕሮግራሙን በበላይነት ይቆጣጠረዋል። አብዛኞዎቹ ይህን አገልግሎት የሚሰጡ አገልጋዮች በቀጠሮ የሚሰሩ በመሆኑ መንገድ ከመጀመርዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ማስያዝ እንዳይረሱ። በዚህ ፕሮግራም ታክስዎን ሊያሰሩ ከፈለጉ የሚከተሉትን ዶክመንቶች ይዘው መሄድ ይኖርብዎታል።

በአቅራቢያችሁ ያለን የነፃ ታክስ ማዘጋጃ ቦታ ለማወቅ ይህን ሊንክ ተጭነው የዚፕ ኮድዎትን ያስገቡና FIND የሚለውን ይጫኑ፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት