12/12/2024
GGh4NjxXAAAuHhY

አርብ 02/16 ምሽት ከባድ ፍንዳታ ያደረሰውና አንድ መኖሪያ ቤትን ሙሉ ለሙሉ ያወደመው እንዲሁም ለአንድ ሰው ነፍስ መጥፋትና ከደርዘን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአካል ጉዳት ያደረሰው ፍንዳታ መንስዔው 500 ጋለን የሚይዝ የፕሮፔን ጋዝ ታንከር ሊክ በማድረጊ እንደሆነ ፖሊስ አስታወቀ።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


አርብ ምሽት 7:38 p.m. ላይ ፖሊስ የ911 ጥሪ እንደደረሰውና ደዋዮች የጋዝ ሽታ በስተርሊንግ 347 Silver Ridge Drive በሚገኘው ቤት አቅራቢያ እንደሸተታቸው ያስታወቁ ሲሆን የአደጋ ተከላካይ ባለሞያዎችም በቦታው ሲደርሱ በቤቱ መሬት ስር የተቀበረ 500 ጋለን የሚይዝ የፕሮፔን ታንከር ሊክ እያደረገ ያገኛሉ።
ወዲያውም ፍንዳታው ተከተለና ከላይ የተጠቀሰውን ጉዳት እንዳደረሰ የላውደን ካውንቲ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ረዳት ቺፍ ዊልያምስ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።
ቺፍ ዊልያምስ አክለውም በርካታ በአካባቢው ያሉ ካውንቲዎች ላደረጉላቸው እርዳታ አመስግነዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት