05/04/2024

ለፒዲዲ በሙዚቃ አቀናባሪነት ያገለግል የነበረው ሮድኒ ጆንስ (ሊል ሮድ) ሻን ኮምብስ በተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃትና ዘለፋ እንደፈጸመበትና የሰራበትን ገንዘብ እንዳልከፈለው በመጥቀስ ክስ መስርቶበታል። የክስ ዶሴው እንደሚያስረዳው ከፒዲዲጋ አብረው ከተከሰሱት መኃል አንዷ የቀድሞ የሞታውን ሬከርድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበረችው ኢትዮጵያ ኃብተማርያም ትገኝበታለች።

ከሳሽ በክስ ዶሴው ላይ እንዳሰፈረው ፒዲዲና አጋሮቹ የተደራጀ ውንብድና ይፈጽሙ እንደነበርና የወሲብ ንግድና በርካታ ህገወጥ አደንዛዥ እጾች ክፍፍል ላይ ተሰማርተው እንደነበር ያትታል። ዋና ተከሳሽ በመኖሪያ ቤቱ በርካታ የተደበቁ ካሜራዎችን እንዳስገጠመና የስራ አጋሮቹ የሆኑትን እነ ኢትዮጵያ ኃብተማርያምና ሌሎች በርካታ ታዋቂ አትሌቶች፤ ፖለቲካኞችና ታዋቂ ግለሰቦችን በድብቅ ይቀርጽ እንደነበር እንደሚያምን ተናግሯል።
ሮድኒ በክስ ወረቀቱ ላይ ለፒዲዲ ካሜራ ማን ሆኖ ባገለገለበት ወቅት በርክታ ህገወት ተግባራት ሲፈጸሙ ቪድዮ እንደቀረጸና መረጃው እንዳለው ተናግሯል።

ሮድኒ ጆንስ በዚህ 70 ገጽ የክስ ዶሴ እንደሚያትተው ፒዲዲና ግብረአበሮቹ ላደረሱበት ጉዳት የ30 ሚልየን ዶላር ካሳ እንዲከፈለው ጠይቋል። ሙሉ የክስ ዶክመንቱን ከስር ማየት ይቻላል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት