12/12/2024
129-harry_byrd_leadership_award-wb

መላው ቨርጂንያ ያሉ ተማሪዎችን ባሳተፈው የሀሪ በርድ ጁንየር ሽልማት የኦስቦርን ፓርክ ሀይስኩል ተማሪ የሆነችው ማራኪ ይልቃልን ጨምሮ ሁለት የፕሪንስ ዊልያም ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲንየር ተማሪዎች አሸነፉ። የዚህ ሽልማት አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 25ሺህ ዶላር የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ይህ ሽልማት በተለይም መልካም ስብዕና ያላቸው፤ በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ፤ የመሪነት ባህርይ የሚያሳዩና ሌሎችን ለማገልገል የማይታክቱ በቨርጂንያ ሃይስኩል ያሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን መርጦ የሚሸልም ፕሮግራም ነው።

ከተሸላሚዎቹ አንዷ ማራኪ ይልቃል ስለሽልማቱና ምን እንደተሰማት ስትጠየቅም “የመጀመሪያው ትውልድ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ተማሪ እንደመሆኔ፣ ይህ ሽልማት ትልቅ ህልም እንዳልምና እና በግቦቼ እንድገፋባቸው በራስ መተማመን እንደሰጠኝ መናገር እችላለሁ። በቀጣዩም ግሎባል ኤንድ ፐብሊክ ሄልዝ በምማርበት ዩኒቨርሲቲ ይህንን ክብር ለማስቀጠል እጓጓለሁ። የወደፊቱ ጊዜም የሰነቀልኝን ለማየት እጓጓለሁ” ብላለች ሲል የፕሪንስ ዊልያም የህዝብ ትምህርት ቤቶች አስታውቋል

ዋሽንግተን ፖስት በሴፕቴምበር 2023 ባወጣው መጣጥፍ ላይ ማራኪና ጓደኞቿ በውድብሪጅ ቨርጂንያ በ2023 ሰመር የእግር ኳስ ግጥሚያ አዘጋጅተው $1500 ዶላር በመሰብሰብ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ሴቶች የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን መግዛት ችለዋል ብሏል።

መረጃውን ያደረሰን ሰለሞን ለገሰን እናመሰግናለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት