12/12/2024
img_3406-1

በቦልቲሞር የሚገኘው የፍራንሲስ ስካት ኪይ ድልድይ ዛሬ ማክሰኛ ለሊት 1:30am ላይ በመርከብ ተገጭቶ ተደርምሷል:: ድልድዩን ያቋርጡ የነበሩ በርካታ መኪኖችም በወቅቱ በድልድዩ ላይ ይሰሩ በነበሩ ሰራተኞች እንዳያልፉ በመከልከላቸው የከፋ አደጋ ሳያጋጥም ቀርቷል:: በሰዓቱ በድልድዩ ላይ የጥገና ስራ ያከናውኑ የነበሩ 6 ሰራተኞች በአደጋው ለህልፈት ተዳርገዋል። የአደጋ ትከላካይ ባለሞያዎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን በመፈለግ ተጠምደዋል:: ድልድዩ የሚገኝበት የአየር ክልልም ከአደጋ ተከላካይ ሄሊኮፕተሮች ውጪ ሌሎች እንዳይበሩ የፌደራል አቪዪሽን አግዷል:: ይህን ተከትሎ የሜሪላንድ ገቨርነር ዌስ ሙር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል::

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት