05/04/2024

ኤፕሪል 8 የሚኖረውን የፀሐይ ግርዶሽ በደንብ ለማየት በተለይም በቀጥታ ፀሐይን በማየት ሊመጣ የሚችለውን የአይን ብርሐን ማጣትን ለመከላከል በማሰብ በየመንደሩ ያሉ የዲሲ የህዝብ ቤተመጽኃፍት መነጽሮችን ከዛሬ ኤፕሪል 2 ጀምሮ በነጻ ያድላሉ፡፡ እኛም ለስራችን አቅራቢያ በሚገኘው አናኮስትያ ላይብረሪ በመገኘት ለልጆቻችን ጨምረን ድርሻችንን ወስደናል፡፡ ይህን አገልግሎት ለማግኘት የላይብረሪው አባል መሆን ወይንም የዲሲ ነዋሪ መሆን አይጠበቅባችሁም፡፡ መነጽሮቹ እስኪያልቁ ማንኛውም ሰው ሄዶ መውሰድ ይችላል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት