
አክሲዮስ ትላንት እንዳስነበበን ከሆነ የሀውስ ሪፐብሊካን አባላት ገፋፍተው ያመጡትንና የዲሲ ካውንስል በ2022 አጽድቆት ተግባራዊ የሆነው የአሜሪካ ዜግነት የሌላቸው የከተማው ነዋሪዎች በከተማው ምርጫ በመራጭነትም በተመራጭነትም መሳተፍ እንዲችሉ የሚፈቅደውን ህግ ለመሻር ለነገ ሐሙስ ሜይ 23 ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የሃውስ ዴሞክራቶች ካሁኑ ይህንን ውሳኔ እንደማይቀበሉ እያሳወቁ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ይህ የፖለቲካ ትዕይንት በተለይም አንዳንድ ዴሞክራቶች በስደተኞች ላይ ለስላሳ አቋም አላቸው ላለመባል ከሪፐብሊካኖችጋ ሊወግኑ እንደሚችሉ እየተገመተ ይገኛል፡፡
የሀውስ ዴሞክራት አመራሮች ግን አባሎቻቸው ይህን ህግ እንዳያጸድቁ በመሪያቸው የማሳቹሴትስ ተወካይ ካትሪን ክላርክ ቢሮ በኩል መመሪያ መላኩ ተሰምቷል፡፡

የማሳቹሴትስ ተወካይ ካትሪን ክላርክ
ምስል ከ፡ https://democraticwhip.house.gov/
በኦክቶበር 2022 በካውንስልሜምበር ብርያን ነዶው ተዘጋጀቶ የቀረእበው የሎካል ሬሲደንትስ ቮቲንግ ራይትስ አክት የተባለውና የአሜሪካ ዜግነት የሌላቸው የዲሲ ነዋሪዎች በአካባቢያዊ ምርጫዎች በመምረጥ መመረጥ መሳተፍ እንዲችሉ የሚያስችላቸው ህግ በብርያን ነዶው ተረቅቆ በካውንስሉ ጸድቆ ነበር።
ይህን ተከትሎም ታዲያ በዋሺንግተን ዲሲ የመጀመሪያው የአሜሪካ ዜግነት የሌለው ሰው ለመንግስት ቢሮ ተመርጧል። ይህም ሰው ኢትዮጵያዊው አቤል አመነ ነው። አቤል በ2023 ማገባደጃ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ካሉትና ዋርዶች በዋርድ 4 አድቫዘሪ ኔይበርሁድ ኮሚሽን ውስጥ በኮሚሽነርነት ለማገልገል በዋርድ 4 ካውንስልሜምበር ጄኒስ ቃለመኃላ ፈጽሞ ኮሚሽነርነቱን ተቀብሎ ነበር፡፡
የአክሲዮስን ዝርዝር ዜና ሊንኩን ተከትለው ያገኙታል፡፡