
በዋሽንግተን ዲሲ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ቅድሚያ መራጮች ድምጻቸውን ካሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ በከተማዋ ባሉ የቅድሚያ መራጮች ጣቢያዎች ድምጻቸውን መስጠት ጀምረዋል፡፡ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ የመጨረሻው ቀንና በአካል መምረጫው ቀን ደሞ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ጁን 4 ነው፡፡
በዚህ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ታዲያ መራጮች ድምጻቸውን በኖቨምበር ምርጫ በፕሬዘዳንትነት ሁለቱን ፓርቲዎች ወክሎ የሚመጣውን መሪ ከመምረጥ ባሻገር በዋርድ 2; 4፣ 7ና 8 ባሉ የዲሲ ካውንስል መቀመጫዎችና በኮንግረስ የዲሲ ተወካዮች ላይም ድምጻቸውን ይሰጣሉ፡፡
ስለ ምርጫው ማወቅ ያለብዎት
- በአካል ቀድመው ለመምረጥ ከሜይ 2 እስከ ጁን 2 ድረስ ለምርጫው ተለይተው በተዘጋጁት ቦታዎች በመሄድ መምረጥ ይችላሉ፡፡
- ዋናው የመጀመሪያ ዙር የምርጫ ቀን ፟ ጁን 4 2024 ከጧት 7 ሰዓት እስከ ምሽት 8 ሰዓት
በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በተለይም በዲሲ ዋርድ 4 የካውንስል አባልነትን ለመያዝ የአሁኗ የካውንስል አባል ጄኒስ ሊዊስና ተቀናቃኞቻቸው ፖል ጆንስና ሊዛ ጎር ይወዳደራሉ፡፡
ባሳለፍነው አመት በተደጋጋሚ ባጋጠማቸው የስትሮክ ህመም ምክኛት በዚህ ምርጫ አልሳተፍም ያሉት የዋርድ 7 ካውንስል አባል ቪንሰንት ግሬይን ቦታ ለመያስ 10 ተወዳዳሪዎች ይፎካከራሉ፡፡
በዚህ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ለመሳተፍ መራጮች የፓርቲ አባል መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡