12/12/2024
img_5865-1

ትላንት 6/28 በነበረው የፕሬዘዳንቶች ክርክር ወቅት ፕሬዘደንት ትራምፕ ካደረጏቸው እጅግ አደገኛ ንግግሮች መሀል አንዱ ስለ ስደተኞች የተናገሩትና ህዝብን በህዝብ ላ በአመፅ ሊያነሳሳ የሚችል ንግግራቸው ጎልቶ ይወጣል:: ትራምፕ ስለ ስደተኞች ይህን ብለዋል “They’re taking Black jobs and they’re taking Hispanic jobs and you haven’t seen it yet but you’re gonna see something that’s going to be the worst in our history,”
አሜሪካ የ Equal Employment Opportunity Act of 1972 በህግ አፅድቃ ማንኛውም ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያለው ሰው ተወዳድሮ ስራ በሚይዝበትን ህግ መሰረት የምትተዳደር እንደመሆኑ ይህ ንግግራቸው መሰተ ቢስ ነው::

እንደ አንድ የስደተኞች ድምፅ ሚዲያ ኢትዮጲክ ይህንን ንግግር በይፋ ታወግዛለች:: እንዲህ ያሉ የግዴለሽ ፖለቲከኞች ንግግር በ2008ና በ2015 በደቡብ አፍሪካ በርካታ ስደተኞች በቁማቸው እንዲቃጠሉ: ሀብት ንብረታቸው እንዲወድም ምክንያት ናቸው::
ይህ የትራምፕ ንግግር የአፍሪካዊ አሜሪካውያንና ስፖኒሾችን በስደተኞች ላይ የሚያነሳሳና ለአሳዛኝ ክስተቶች በር የሚከፍት ብመሆኑ በይፋ እናወግዛለን!!

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት