ከነገ ጁላይ 9 እስከ ሐሙስ ጁላይ 11 2024 በዋሽንግተን ዲሲ ኮንቬንሽን ሴንተር በሚደረገው 75ኛው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን አባል ሀገራት (NATO) ስብሰባ አማካኝነት በርካታ በዋሽንግተን ዲሲ ዳውንታውን አካባቢ ያሉ መንገዶች ለተሽከርካሪና ለእግረኛ እንደሚዘጉ የዲሲ ፖሊስና የዲሲ ከንቲባ በጋራ ባዛጋጁት የፕሬስ ኮንፍረንስ አሳውቀዋል።
ይህ የመሪዎችና የሀገራት ልኡካን ስብሰባ በዲሲ ሲደረግ ከ25 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው እንደሆነም ተነግሯል።
የዚህን ስብሰባ ደህንነት ለማስጠበው በርካታ የሴኩሪቲና ደህንነት ተቋማትን ያቀፈ ግብረሀይልም ወደስራ ገብቷል።
ከዛሬ ሰኞ ጁላይ 8 ጀምሮ ስብሰባው እስኪያልቅ ድረስም ለመኪና ማቆሚያ የተከለከሉ መንገዶች፤ ለአሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንግዶች እንዲሁም ለእግረኞች የተከለከሉ መንገዶችን ካርታ የዲሲ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
በዋናነትም እንዚህ ዝግ መንገዶች በዳውንታውን ናሽናል ሞል አቅራቢያ በሚገኘው የሜሎን የመሰብሰቢያ አዳራሽና ዋይት ኃውስ ዙሪያ እንደሆነ ተነግሯል።
ከመንገዶች በተጨማሪም 2 የሜትሮ ጣቢያዎች ይዘጋሉ። ለትራፊክ በሚዘጉ መንገዶች አማካኝነት ከ20 በላይ የሚሆኑ የሚተሮ ባስ መስመሮች የመንገድ ልዋጭ እንዲያደርጉ እንደሚገደዱም ተነግሯል። በርካታ ቀጣሪዎችም ሰራተኝቻቸው የሚችሉ ከሆነ ከቤታቸው እንዲሰሩ ፍቃድ ሰተዋል።
የሚዘጉ መንገዶችን ዝርዝር ለማወቅ ከስር ያሉትን ካርታዎች ይመልከቱ።
የኖርዝ አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን አባል አገራት መሪዎችም ከዛሬ ጀምሮ ዋሽንግተን ዲሲ መግባት ጀምረዋል።