Customize Consent Preferences

We use cookies to help you navigate efficiently and perform certain functions. You will find detailed information about all cookies under each consent category below.

The cookies that are categorized as "Necessary" are stored on your browser as they are essential for enabling the basic functionalities of the site. ... 

Always Active

Necessary cookies are required to enable the basic features of this site, such as providing secure log-in or adjusting your consent preferences. These cookies do not store any personally identifiable data.

No cookies to display.

Functional cookies help perform certain functionalities like sharing the content of the website on social media platforms, collecting feedback, and other third-party features.

No cookies to display.

Analytical cookies are used to understand how visitors interact with the website. These cookies help provide information on metrics such as the number of visitors, bounce rate, traffic source, etc.

No cookies to display.

Performance cookies are used to understand and analyze the key performance indexes of the website which helps in delivering a better user experience for the visitors.

No cookies to display.

Advertisement cookies are used to provide visitors with customized advertisements based on the pages you visited previously and to analyze the effectiveness of the ad campaigns.

No cookies to display.

የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ(5)

በእለተ አርብ ኤፕሪል 5 ምሽት 11፡21 ላይ የዲሲ ፖሊስ የስልክ ጥሪ ደርሶት ወደ 1300 ፒበዲ ስትሪት አቅራቢያ ባለ አፓርታማ ውስጥ በጩቤ ተወግቶ የነበረውን የ53 ዓመቱን ጎልማሳ ፋሲል ተክለማርያምን ያገኙታል፡፡ በወቅቱ ለአደጋው የደረሱት የዲሲ ፖሊስና አምቡላንስ የመጀመሪያ አደጋ ደራሾች ታዲያ ፋሲል በደረሰበት ጉዳት ለህልፈት እንደተዳረገና ከሞተም አራት ቀን እንዳለፈው አረጋግጠዋል፡፡ በወቅቱም ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ያለው ሰው እንዲጠቁም የ25000$ ሽልማት እንዳዘጋጀ አስታውቆ ነበር፡፡

ጁን 21 ላይ ታዲያ ወንጀሉን ሲመረምር የነበረው የዲሲ ፖሊስ በፋሲል ህልፈት ጠርጥሬዋቸዋለሁ ያላቸውን የ22 ዓመቷን ቲፋኒ ቴይለር ግሬይና የ19 ዓመቷን ኦድሪ ሚለርን በቁጥጥር ስር እንዳዋለና ለፍርድ እንዳቀረባቸው አሳውቋል፡፡ የክስ መዝገባቸው እንደሚያሳየውም ፋሲል ጭንቅላቱና ሆዱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ለህልፈት እንደተዳረገና በተጨማሪም በርካታ ቁስልና መላላጥ እግሩና እጁ ላይ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአስከሬን ምርመራ እንደተረጋገጠው ፋሲል ለህልፈት በተዳረገበት ወቅት የፋሲል አውራ ጣት እንደተቆረጠ ታውቋል፡፡ የተቆረጠው አውራጣትና የፋሲል ስልክ፤ ላፕቶፕና ሌሎች ማናቸው ኤሌክትሮኒክሶች በአፓርታማው እንዳልተገኙ ታውቋል፡፡

በፖሊስ ምርመራ የተገኙና ለፍርድ ቤት የቀረቡ ምስሎችና ዶክመንቶች እንደሚያሳዩትም ፋሲልና ተጠርጣሪ ኦድሪ ሚለር ከመሞቱ 4 ቀን በፊት ወደ አፓርታማ አብረው ሲገቡ እንደታዩ የሴኩሪቲ ካሜራ ላይ ታይተዋል፡፡ ለፖሊስ ከተላኩ በርካታ ጥቆማዎችና ከበርካታ የአይን ምስክሮች እንደተሰማውም ፋሲል ተክለማርያም የ22 ዓመቷ ቲፋኒ ቴይለር ግሬይ ሹገር ዳዲ እንደነበር ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም ምስክሮች ከፋሲል ህልፈት በኋላ ተጠርጣሪዋ የሟችን አውራጣት በመጠቀም ገንዘብ ከካሽ አፕ አካውንቱ ስታወጣ እንደነበርና ለኡበር፤ ለአደንዛዥ ዕጽና ለአልክሆል ስትከፍል እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ግሬይና ሚለር በመሳርያ በታገዘ የአንደኛ ደረጃ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡

ለጥቆማው ራስ አስራትንና ጆን ጉድማንን እናመሰግናለን፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.