Screenshot 2024-08-12 at 12.54.56

እንደ ሴክሽን 8 ያሉ የአፎርደብል ቤቶችን በመገንባትና ማከራየት የሚታወቀው ጁብሊ ሀውሲንግ በዋሽንግተን ዲሲ አዳምስ ሞርጋን አካባቢ ባሉት አፓርታማዎች ተጠባባቂዎችን መመዝገብ እንደሚጀምር ዛሬ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ይህ ምዝገባ ተመዝጋቢዎችን እንደ አመጣጣቸው የሚያስተናግድ ሲሆን ቀድሞ የመጣ ቀድሞ የሚመዘገብ እንደሆነም ተነግሯል።

ምዝገባው የሚደረገው ረቡዕ ኦገስት 28 2024 ከጧት 10 ሰዓት እስከ ከሰዓት 4 ሰዓት ብቻ ነው። የምዝገባው ቦታም በ1640 Columbia Road NW Washington DC 2009 በሚገኘው ፌስቲቫል ሴንተር እንደሆነ ተነግሯል።

ተቋሙ ከኢፊሸንሲ ጀምሮ እስከ ባለ 3 መኝታ አፓርታማዎች ተጠባባቂዎችን እንደሚመዝግብ በማስታወቂያው አስታውቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.