በሜሪላንድ አመታዊው ከቀረጥ ነፃ ግብይት ከኦገስት 11-17 ድረስ ይከናወናል። በዚህ አንድ ሳምንት የጊዜ ገደብ ውስጥ ዋጋቸው ከ100$ በታች የሆኑና የተፈቀደላቸው ጫማዎችና አልባሳት ከሽያጭ ታክስ ነፃ ይሆናሉ። የሜሪላንድ የቀረጥ ነፃ ህግ ይህንን የቀረጥ ነፃ እድል ለመጠቀም ሰዎች ያለገደብ መግዛት እንዲችሉ ይፈቅዳል። በተጨማሪም የተማሪዎች ቦርሳ እስከ 40$ ድረስ ከቀረጥ ነፃ ነው።
በዚህ ወቅት ቅናሽ የሚደረግባቸው ቁሶች በዋናነት ሹራቦች፤ ሸሚዞች፤ ጂንስ፤ ቀሚሶች፤ ገዋኖች፤ የውስጥ አልባሳት፤ ቀበቶአ ጫማዎችን የሚያጠቃልል እንደሆነ ተነግሯል።
በዚህ ወቅት ታዲያ ሁሉም ሸቀጦች ላይ ቅናሹ እንደማይሰራ የተገለጸ ሲሆን በዋናነትም ጌጣጌጦች፤ ሰዓት፤ የሰዓት ዘለበት፤ የእጅ ቦርሳዎች፤ መሀርቦች፤ ዣንጥላ፤ ስካርፎች፤ ከረባትና የመሰሳሰሉትን አያካትትም።
ለበለጠ ዝርዝርና ተደጋግመው ለሚነሱ ጥያቄዎች የሜሪላንድ መንግስት ያዘጋጀውን ዶክመንት ይህን ተጭነው ማንበብ ይችላሉ።