GUdkHQ_a8AAkSXt

የትሮፒካል ስቶርም ዴቢ ርዝራዥ በዲሲና አካባቢው ዛሬና ነገ አካባቢያችንን በዝናብና ጎርፍ፤ ኃይለኛ ንፋስና እንዲሁም የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ደሞ ቶርኔዶ ሊያስከትል እንደሚችል የብሄራዊ ሜትሮሎጂ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የዲሲ ዲፓርትመንት ኦፍ ቢውልዲንግ ዛሬ ኦገስት 8ና ነገ ኦገስት 9 ይኖራል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ተፈጥሯዊ ክስተት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ እንዲቻል ሁሉም የዲሲ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያስገነዝብ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም እንደተገለጸው የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ከ24᎒6 ሰዓት የሚዘልቅ ዝናብና ንፋስ ሊያደርሰው የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ማንኛውም ባለንብረት ንብረቱን እንዲጠብቅ እንዲሁም ማንኝዐውም አዲስ ግንባታ የሚያደርግ ሰው ቁሳቁሱን በአግባቡ እንዲጠብቅና በንፋስና ጎርፍ ተወስዶ አደጋ እንዳያደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ተናግሯል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.