ፖሊስ ተፈላጊው እንደተገኙ አስታውቋል፡፡
የሞንጎምሪ ካውንቲ ዛሬ ኦገስት 20 ባወጣው ማስታወቂያው የ77 አመት አዛውንት የሆኑትን አቶ አምበሶ መስቀሉን አፋልጉኝ ብሏል።
አቶ አምበሶ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ሰኞ ኦገስት 19 2024 በግምት ከሰዓት 2፡30 pm አካባቢ በ 3200 ኦቶሞቢል ቡሌቫርድ አካባቢ ነው ተብሏል።
አቶ አምበሶ ቁመታቸው 5ጫማ ከ7ኢንች ነው። ክብደታቸው 150 ፓውንድ ሲሆን ጸጉራቸውና ጺማቸው ሽበት ያለበት ጠይም ሰው ናቸው።
አቶ አምበሶ በወቅቱ የሜሪላንድ ታርጋ ቁጥር 8GG6560 የሆነ የ2025 ሆንዳ ሲቪክ ሊያሽከረክሩ እንደሚችሉ በመግለጫው ተጠቁሟል።
በወቅቱ አቶ አምበሶ እጅጌ ጉርድ ሸሚዝና ቤዥ ከለር ሱሪ አድርገው እንደነበር ተነግሯል።
አቶ አምበሶ ያሉበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር 301-279-8000 በመደወል ሪፖርት እንዲያደርግ ተጠይቋል።