12/12/2024
Election 2024 Senate Virginia Debate

FILE - This combination file photos shows, from left,Sen. Tim Kaine, D-Va, on Sept. 24, 2020, on Capitol Hill in Washington, and Hung Cao, July 16, 2024, in Milwaukee. (AP Photo/Susan Walsh, left, J. Scott Applewhite)

ኖርፎክ ቨርጂንያ-አሶሼትድ ፕሬስ – ኦክቶበር 2 2024፤ በቨርጂንያ ለዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት መቀመጫ እየተወዳደሩ የሚገኙት የዴሞክራቱ ሴናተር ቲም ኬይን እና የሪፐብሊካኑ ሁንግ ካኦ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ትላንት ረቡዕ ክርክር አድርገዋል፡፡ በኖርፎክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተከናወነውና ለአንድ ሰዓት በዘለቀው በዚህ ክርክር ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ከህገወጥ ስደተኞች እስከ ኢኮኖሚና ከውጭ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ስለሚጣል ታሪፍ ተከራክረዋል፡፡

የሪፐብሊካኑ ካኦ የኮቪድ ክትባት በወታደር ምልመላና ቅጥር ግዴታ መሆኑን አጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን በተጨማሪም በእኩልነትና አካታችነት (diversity, equity and inclusion) ስም የሚደረግ ምልመላንም ተቃውመዋል፡፡

የዴሞክራቱ ሴናተር ኬይን በበኩላቸው ይህ ተቃውሞ ከዋናውና አንገብጋቢው ጉዳይ የሚደረግ ሽሽት እንደሆነና ዋናው ተግዳሮት እስካሁን 1 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ብቻ በውትድርና ውስጥ እንዳለና አሜሪካውያንን በውትድርና መሳተፍ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ማስቻል እንደሆነና ጠቁመዋል፡፡

U.S. Sen. Tim Kaine of Virginia , left, debates Republican challenger Hung Cao at Norfolk State University in Norfolk, Va., on Wednesday Oct. 2, 2024. (Nextstar/WAVY-TV via AP, Pool)

በተጨማሪም የቀድሞው ፕሬዘደንት ትራምፕ ከውጭ በሚመጡ ሸቀጦች ላይ አደርገዋልሁ ስላሉት ቀረጥ አስመልክተው ሁንግ ካኦ እንደሚደግፉትና አሜሪካውያን አምራቾችን በቀረጥ ከምንቀጣ ከውጭ ምርት የሚያስገቡትን ቢያስከፍሉ እንደሚመርጡ ተናግረዋል፡፡

ሴናተር ቲም ኬይን በበኩላቸው ይህ የትራምፕ ቀረጥ በመገልገያ ቁሶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ንረት እንደሚያስከትልና እንደሚቃወሙት ተናግረዋል፡፡

ወረቀት የሌላቸውን ስደተኞች በሚመለከት የጅምላ ዲፖርቴሽን እንደሚደግፉ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሪፐብሊካኑ ሁንግ ካኦ በህገወጥ መንገድ ከገባችሁ ስራዓቱን አፋልሳችኋል ሲሉ ተናግረው ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡ የዴሞክራቱ ሴናተር ኬይን በበኩላቸው በህገወጥ መንገድ ለገቡ ስደተኞች ምህረት ይደረግ በሚለው እንደማይስማሙ ኝ በጅምላ ዲፖርት ማርደግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚጎዳ ተናግረዋል፡፡

የሪፐብሊካኑ ሁንግ ካኦ በቀድሞው ፕሬዘደንት ትራምፕ ድጋፍ የተቸራቸው ሲሆን የፖለቲካ ተንታኞች ኝ የማሸነፍ እድላቸው ጠባብ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የቨርጂንያ መራጭ በአብዛኛው መሀከል ላይ (Moderate) በመሆኑ ነው፡፡  በ2018 ምርጫ ሴናተር ቲም ኬይን በ16 ፐርሰንት በማሸነፍ ነው የሴኔት አባል የሆኑት፡፡ ዘገባውና ምስሎቹ የአሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት