12/12/2024
ለመምረጥ ይመዝገቡ (1)

አመታዊው የዲሲ የስራ ፈጣሪዎችና የቴክኖሎጂ ሳምንት በመጪው ሰኞ ኦክቶበር 21 ጀምሮ እስከ አርብ ኦክቶበር 25 በዋሽንግተን ዲሲ በተለያዩ ቦታዎች ይከናወናል። በዚህ ለ5 ቀን በሚቆይ ፕሮግራም ላይ ከ300 በላይ ሰዎች ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ከ150 በላይ ዝግጅቶችና ከ7000 በላይ ታዳሚዎች ይኖሩታል ተብሏል።

ይህ ፕሮግራም ሰኞ በኔቪ ያርድ አቅራቢያ ባለውና በ700 M St SE, Washington, DC 20003 በሚገኘው በካፒታል ተርንራውንድ ከጧቱ 9 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ይሆናል። በመክፈቻው ላይ የዲሲ ከንቲባ መርቀው የሚከፍቱት ሲሆን ለዲሲ ስራፈጣሪዎችና የቴክኖሎጂ ማህበረሰብም ልዩ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሏል።

ይህ ፕሮግራም በዋናነት በ4 ዘርፎች ተከፍሏል። እነሱም የጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፤ በማደግ ላይ ያሉ ስራ ፈጣሪዎች፤ አዳዲስ የቴክኖሎጂና የኤ.አይ መድረክና ለበጎ የተቋቋሙ ተቋማት መድረክ ናቸው።

በዚህ ፕሮግራም ላይ በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ የሚንቀሳቀሱ ስራ ፈጣሪዎች፤ የመንግስት ባለስልጣናት፤ ኢንቬስተሮች፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሌሎችም ይገኙበታል። ሙሉ ፕሮግራሙን ለማየት ይህን ይጫኑ:: የመግቢያ ትኬቱን ለመግዛት ይህን ይጫኑ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት