12/12/2024
ማንን ሊመርጡ አስበዋል

ከቢ ጂ ኢ፤ ከዴልማርቫ ፓወር፤ ከፔፕኮና ከፖቶማክ ኤዲሰን መብራታቸውን ሲያገኙ የነበሩ ደንበኞች ከኦክቶበር 2024 ጀምሮ የዋጋ ታሪፍ ለውጥ እንደሚኖራቸው ተነግሯል፡፡ በአዲሱ የዋጋ ተመን መሰረት የቢ ጂ ኢ ደንበኞች በኪሎዋት-ኧወር ከ0.09472$ ወደ 0.10405$ ያድጋል፡፡ የዴልማርቫ ደንበኞች ደሞ በኪሎዋት-ኧወር ከ0.09651$ ወደ 0.09962$ ያድጋል፡፡ የፔፕኮ ደንበኞች ሂሳብም በኪሎዋት-ኧወር ከ0.09262$ ወደ 0.10348$ ከፍ ይላል፡፡ የፖቶማክ ኤዲሰን ደንበኞች ታሪፍ በኪሎዋት-ኧወር ከ0.08856$ ወደ 0.09320$ ያድጋል

አመቱን ሙሉ የዋጋ መዋዠቅ ሊኖር እንደሚችልና ይህ ዋጋ በትንሹ ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ እንደሚችልም የሜሪላንድ ፒፕል ካውንስል ቢሮ አስረድቷል፡፡

በየመኖርያ ቤትዎ እየመጡ የመብራት ቅናሽ እናረጋለን ብለው ላልተፈለገ ወጪ የዳረጓችሁ ካሉ ወደ ዋናው የአገልግሎት ሰጪ በመደወል አገልግሎታችሁን ማቋረጥ እንደምትችሉም ቢሮው የላከው መረጃ ያሳያል፡፡

በተጨማሪም ቢሮው የዚህን ወር የጋዝ ዋጋ ይፋ አድርጓል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት