12/12/2024
ማንን ሊመርጡ አስበዋል (1)

የታሪካዊ የጥቁሮች ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ከሚከበሩ በዓላት አንዱና ዋነኛው የዩንቨርስቲዎቹ የቀድሞ ተማሪዎች በየዓመቱ የሚሰባሰቡበትና የሆም ካሚንግ በአል ዋነኛው ነው። የሆም ካሚንግ በዓል በአብዛኛው ለሳምንት ይዘልቃል።

በነዚህ በዓላት ላይ የአሜሪካን ኳስ ጨዋታዎች፤ የጎዳና ትርዒቶች፤ የሚዚቃ ኮንሰርቶች፤ የተማሪዎች ሪዩኒየን ፕሮግራሞች፤ የተለያዩ ፍራተርኒቲዎችና ሶሮሪቲዎች ፕሮግራሞች ይከናወናሉ።
የዲሲ ኃዋርድ ዩኒቨርሲቲም ታዲያ ዘንድሮ ለ100ኛ ጊዜ Yard of Fame ተብሎ የሚያከብረው የሆም ካሚንግ በዓሉን ካለፈው እሁድ ኦክቶበር 12 ጀምሮ ሲያከብር የቆየ ሲሆን ዋናው ክብረ በዓል ግን ዛሬ አርብ ኦክቶበር 18ና ነገ ቅዳሜ ኦክቶበር 19 በደማቁ ይከበራል።

ከዚህ ቀደም በነዚህ የሆም ካሚንግ በዓላት ላይ እንደ ጄይ ዚ ያሉ ትልልቅ አርቲስቶች ተሳትፈውበታል። የዘንድሮው መቶኛው በዓል በትልቁ እንደሚከበርም ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

ከነዚህ ፕሮግራሞች በተለይም በጉጉት የሚጠበቀው የኃዋርድ ባይሰንና የቴኔሲ ታይገር የኳስ ግጥሚያ ሲሆን ጨዋታው ቅዳሜ ከሰዓት 3፡30 ላይ በግሪን ስታዲየም ይከናወናል።

ይህን ታላቅ ፕሮግራም በማስመልከት ታዲያ የዲሲ ፖሊስ የሚከተሉት መንገዶች ከዛሬ አርብ ኦክቶበር 18 እኩለ ቀን ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ኦክቶበር 19 ምሽት 11፡59pm ለመኪና ማቆሚያ ዝግ እንደሆኑ አስታውቋል።

  • 6th Street, NW from Girard Street, NW to College Street, NW
  • Howard Place, NW from Georgia Avenue, NW to 6th Street, NW
  • Girard Street, NW from Georgia Avenue, NW to 6th Street, NW
  • Fairmount Street, NW from Georgia Avenue, NW to 6th Street, NW

በተጨማሪም ከቅዳሜ ኦክቶበር 19 2024 ከጧት 6፡00am ጀምሮ እስከ ምሽት 11፡59pm ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ላይ መኪና ማቆም ክልክል ነው።

  • Georgia Avenue from Gresham Place to Florida Avenue, NW
  • Barry Place from Sherman Avenue to Georgia Avenue, NW
  • 8th Street from Barry Place to V Street, NW
  • W Street from 9th Street to 8th Street, NW
  • W Street from Georgia Avenue to 4th Street, NW
  • 4th Street from W Street to McMillian Drive, NW

የሚከተሉት መንገዶች ደሞ ቅዳሜ ኦክቶበር 19 2024 ከጧት 7፡00am ጀምሮ እስከ ምሽት 11፡59pm ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

  • Georgia Avenue from Gresham Place to Florida Avenue, NW (ወደ ኃዋርድ ሆስፒታል ለሚገቡ መኪኖች መንገዱ ጆርጂያና ፍሎሪዳ ወይንም ጆርጂያና ቪ ስትሪት ላይ ክፍት ይሆናሉ)
  • Barry Place from Sherman Avenue to Georgia Avenue, NW
  • 8th Street between Barry Place and V Street, NW
  • W Street from 9th Street to 8th Street, NW
  • College Street from 4th Street to 6th Street, NW
  • Bryant Street from 4th Street to 6th Street, NW
  • W Street from 4th Street to Georgia Avenue, NW
  • 5th Street from Gresham Place to McMillan Drive, NW
  • 5th Street from W Street to V Street, NW
  • 4th Street from McMillan Drive to W Street, NW

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት