የዩናይትድ ስቴትስ በሽታ መቆጣጠር ባለስልጣን መስሪያ ቤት (ሲ.ዲ.ሲ) ዛሬ እንዳሳወቀው ከሆነ በበርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች በሚገኙ የኳርተር ፓውንደር በርገር ይተመገቡ ሰዎች ኢ. ኮላይ በተባለ የበሽታ አማጭ ጀርም ለህመም መዳረጋቸውንና በተለይም በኮሎራዶ አንድ ሰው ለጽኑ የኩላሊት በሽታ ሲዳረግ ሌላ አዛውንት ደሞ ለህልፈት እንደተዳረጉ ተነግሯል።
በሽታው እስካሁን በኦርላንዶ፤ ሞንታና፤ ዋዮሚንግ፤ ዩታ፤ ኮሎራዶ፤ ኔብራስካ፤ ካንሳስ፤ አዮዋ፤ ሞንታናና ዊስኦንሲን የተገኘ ሲሆን ሲዲሲ በሌሎች በርካታ ግዛቶችም ሊኖር እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለው አሳውቋል።
ይህን ተከትሎም በሽታው ታይቶባቸዋል በተባሉ ግዛቶች በሙሉ ባሉ ማክዶልድ ምግብ ቤቶች የኳርተር ፓውንደር በርገር እንዳይሸጥ ተደርጓል። ማክዶናልድ የወረርሺኙን መንሲዔ ለማግኘት ከሲዲሲጋ እየሰራ እንደሆነና በበርገሮቹ የሚጠቀማቸውን የተከተፉ ጥሬ ሽንኩርቶች በጊዜያዊነት እንዳስወገደ ተነግሯል።
ሲዲሲ አክሎም ማንኛውም ሰው ማክዶናልድ ምግብ ቤት ከተመገበ በኋላ የኢኮላይ ምልክቶችን ካሳየ በአስቸኳይ የጤና ባለሞያውጋ እንዲሄድ መክሯል።
በኢኮላይ ጀርም የተያዘ ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ዋነኞቹ
- ተቅማጥና ከ102 ዲግሪ በላይ ትኩሳት
- ከ3 ቀን በላይ የሆነው ተቅማጥ
- ደም የተቀላቀለበት ተቅማጥ
- የማያባራ ትውከት
- የሰውነት መድረቅ (ውኃ ማጣት)
- ከባድ የሆድ ቁርጠት
እነዚህ ምልክቶች ባክቴርያው ወደሰውነት ከገባ ከ3-4 ቀናት ውስጥ ይከሰታሉ ተብሏል።
ይህን ተከትሎም የማክዶናልድ የስቶክ ማርኬት ዋጋ ይህን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ በ5.96% ወርዷል።