ባሳለፍነው ቅዳሜ ኦክቶበር 19 2024 አዲስ በተከፈተው የሞንጎምሪ ካውንቲ ኮሚውኒቲ ኮሌጅ ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና ወላጆች ኦፕን ሃውስ ፕሮግራም ነበረው። የዚህ ፕሮግራም ዋነኛ አላማ የነበረው ደሞ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዴት የሃይስኩል ዲፕሎማቸውንና የኮሌጅ ክሬዲት በአንድ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ገለጻ ለመስጠት ነው።
የኮሌጁ የዱዋል ኢንሮልመንት ፕሮግራምን የሚከታተለው ክፍል የአካዴሜክ ኢኒሼቲቭ ዳይሬተር የሆኑት አኪማ ሮጀርስ በዕለቱ ለመጡ ሰዎች ማብራሪያ ሰተዋል። በማብራሪያው ላይ እንዳስቀመጡትም ዱዋል ኢንሮልመንት ፕሮግራም ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና የኮሌጅ ተማሪ መሆን ይችላሉ።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነ ኮሌጁ አስፈላጊውን አማካሪዎች በመመደብ ተማሪዎች በ2 አመት የኮሌጅ ክሬዲታቸውንና የሀይስኩል ዲፕሎማ ማግኘት እንዲችሉ እንደሚያግዝ ያስረዱ ሲሆን የማመልከቻ ጊዜውም ኖቨምበር 1 እንደሆነ አክለው ጠቅሰዋል። ይህንን የኮሌጅ ክሬዲት የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የሚቀበሉት ሲሆን ይህም ተማሪዎች በነጻ የወሰዷቸውን ኮርሶች በማቃለል የትምህርት ብድራቸውን ዕዳ ሊቀንሱ እንደሚችሉ ተነግሯል። ሆኖም አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች እነዚህ ክሬዴቶች እንደማይቀበሉና ይህንን ወላጆችና ተማሪዎች አስቀድመው ማጣራት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል። በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ የሚሹ ልጆች ካሉዎት በዚህ ሊንክ ሄደው መመዝገብ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ደሞ የኮሌጁን ድረገጽ ይህን በመጫን ማግኘት ይችላሉ።