በቨርጂንያ ፌርፋክስ ካውንቲ የአፎርደብል ሃውሲንግ ቤቶች ለማግኘት የሚሹ ሰዎች ኦንላየን ሬንት ካፌ ላይ በመግባት በተጠባባቂነት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በዚህ ዙር የተጠባባቂ ነዋሪዎችን የሚመዘግቡት አራት አፓርታማዎች ሲሆኑ ሁለቱ ለማንኛውም ዕድሜው ከ18 ኣመት በላይ ለሆነ ሰው እና የተቀሩት ሁለቱ ደሞ ዕድሜያቸው ከ62 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች ብቻ ነው፡፡ እነዚህ አፓርታማዎች ባለ ስቱዲዮ፤ ባለ አንድ መኝታ፤ ባለ ሁለት መኝታና ባለ ሶስት መኝታ ሲሆኑ ዝርዝራቸው እንደሚከተለው ነው፡፡
ከ18 ዓመት በላይ ያለ ማንኛውም አዋቂ ማመልከት የሚችልባቸው መኖሪያዎች
- Coralain Gardens, studio, one, and two-bedroom apartments 7435 Arlington Blvd., Falls Church, VA 22042
- The Residences at North Hill, one, two, and three-bedroom apartments 7230, 7240, 7250, and 7255 Nightingale Lane, Alexandria, Virginia 22306
ከ62 ዓመት በላይ ያለ ማንኛውም አዛውንት ማመልከት የሚችሉባቸው መኖሪያዎች
- Little River Glen, one-bedroom apartments 4001 Barker Court, Fairfax, VA 22032
- The Senior Residence at North Hill, one and two-bedroom apartments, 7245 Nightingale Lane, Alexandria, Virginia 22306
ማመልከት የሚፈልጉ ሬንትካፌ ላይ በመግባት ማመልከት ይችላሉ፡፡ ለማመልከት ድጋፍ ወይንም እገዛ የሚፈልጉ ደሞ ካውንቲው ጋ በ 703 246 5100 በመደወል ወይንም ወደፌርፋክስ ካውንቲ ቤቶች ልማት ቢሮ 3700 Pender Drive in Fairfax, VA. በአካል በመሄድ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለማመልከት ይህን ሊንክ ተጭነው ወደ ሬንት ካፌ ድረ ገጽ ይሂዱ፡፡
የበለጠ መረጃ ለማግኘት የካውንቲው ቤቶች ልማት ድረ ገጽ ላይ ገብተው ማግኘት ይችላሉ፡፡
ዜናውን ያደረሰችንን ትህትና ሞገስን እናመሰግናለን፡፡