በሜሪላንድ በጊዜ መምረጥ ለሚሹ ከዛሬ ኦክቶበር 24 2024 ጀምሮ መምረጥ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ የሜሪላንድ መራጮች አስቀድመው ካልተመዘገቡና የመራጭነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሆነ በምርጫ ጣቢያዎች ተመዝግበው ድምጻቸውን መስጠት ይችላሉ፡፡ እንደ ሜሪላንድ የምርጫ ቦርድ ከሆነ በሜሪላንድ በጠቅላላው 87 የምርጫ ጣቢያዎች ከዛሬ ጀምሮ መራጮችን ያስተናግዳሉ፡፡
በአቅራቢያዎ ያለውን የመምረጫ ጣቢያ ለማወቅ ከስር ያለውን የሜሪላንድ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀውን ዝርዝር ይመልከቱ፡፡