12/12/2024
Add a heading

ምክትል ፕሬዘደንት ካማላ ሀሪስ ነገ ኖቨምበር 5 የምርጫ ውጤቶችን ለመመልከት የምርጫ ባልደረቦቻቸውን ይዘው ከታሪካዊ የጥቁሮች ዩኒቨርስቲ አንዱ በሆነው በዋሽንግተን ዲሲው ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ እንደሚከትሙ ተነግሯል፡፡ ይህንን ተከትሎም ጆርጂያ አቬኑን ጨምሮ በርካታ መንገዶች ለመኪና ማቆሚያነትም ይሁን ለትራፊክ ዝግ ሆነዋል፡፡

የዋሽንግተን ዲሲ የህንጻ ግንባታ ቢሮም በሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያሉ ማናቸውም የግንባታ ስራዎች እንዲቆሙ አዟል፡፡ የተወሰኑት የትራንስፖርትና ትራፊክ እግዶች ከትላንት ዕሁድ 11/3 ጀምሮ ተግባራዊ የሆኑ ሲሆን ቀሪዎቹ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

በዚህ ወቅት የሀዋርድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ለተገልጋዮች ክፍት እንደሚሆንና ታካሚዎች በጆርጂያና ፍሎሪዳ አቬኑ መግቢያ መጠቀም እንደሚችሉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

እንደፖሊስ መረጃ ከሆነ የሚከተሉት መንገዶች በሙሉ ከትላንት ዕሁድ ኖቨምበር 3 ጀምሮ እስከ እሁድ ኖቨምበር 10 ንጋት 6am መኪና እንዳይቆምባቸው ተከልክለዋል::

  • Gresham Place from 5th Street to Georgia Avenue, NW
  • Girard Street from Georgia Avenue to 6th Street, NW
  • Fairmont Street from Georgia Avenue to 6th Street, NW
  • Euclid Street from Sherman Avenue to Georgia Avenue, NW
  • Howard Place from Georgia Avenue to 6th Street, NW
    Barry Place from Sherman Avenue to Georgia Avenue, NW
  • College Street from 6th Street to 4th Street, NW
  • 300 block of College Street, NW
  • Bryant Street from Georgia Avenue to 2nd Street, NW
  • W Street from 9th Street to 8th Street, NW
  • W Street from Georgia Avenue to 2nd Street, NW
  • V Street from Florida Avenue to Georgia Avenue, NW
  • 9th Street from Euclid Street to U Street, NW
  • 8th Street from Barry Place to V Street, NW
  • Georgia Avenue from Harvard Street to Florida Avenue, NW
  • 6th Street from Girard Street to W Street, NW
  • 5th Street from V Street to W Street, NW
  • 4th Street from V Street to McMillan Drive, NW

በዚህ ወቅት በነዚህ መንገዶች ላይ መኪናውን አቁሞ የሄደ ሰው የቅጣት ትኬት ከማግኘት ባለፈ መኪናው ቶው እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡

ከዛሬ ሰኞ ምሽት 7pm ጀምሮ ደሞ የሚከተሉት መንገዶች በሙሉ ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን ለምን ያህል ጊዜ ተዘግተው እንደሚቆዩ ፖሊስ በሂደት እንደሚያሳውቅ ተነግሯል፡፡

  • Gresham Place from 5th Street to Georgia Avenue, NW  
  • Girard Street from Georgia Avenue to 6th Street, NW 
  • Fairmont Street from Georgia Avenue to 6th Street, NW 
  • Euclid Street from Sherman Avenue to Georgia Avenue, NW 
  • Howard Place from Georgia Avenue to 6th Street, NW 
  • Barry Place from Sherman Avenue to Georgia Avenue, NW 
  • College Street from 6th Street to 4th Street, NW  
  • 300 block of College Street, NW  
  • Bryant Street from Georgia Avenue to 2nd Street, NW  
  • W Street from 9th Street to 8th Street, NW  
  • W Street from Georgia Avenue to 2nd Street, NW 
  • V Street from Florida Avenue to Georgia Avenue, NW  
  • 9th Street from Euclid Avenue to U Street, NW  
  • 8th Street from Barry Place to V Street, NW 
  • Georgia Avenue from Harvard Street to V Street, NW 
  • 6th Street from Girard Street to W Street, NW  
  • 5th Street from V Street to W Street, NW  
  • 5th Street from Gresham Place, NW to McMillan Drive, NW 
  • 4th Street from V Street to McMillan Drive, NW  

በተጨማሪም የሚከተሉት መንገዶች ከዛሬ ሰኞ ኖቨምበር 4 ምሽት 7pm  ጀምሮ ለነዋሪዎች ብቻ ክፍት እንደሚሆኑና ፖሊስ ነዋሪዎችን እየመረጠ እንደሚያሳልፍ ተነግሯል፡፡

  • Gresham Place from Georgia Avenue to Sherman Avenue, NW  
  • Girard Street from Georgia Avenue to Sherman Avenue, NW 
  • Fairmont Street from Georgia Avenue to Sherman Avenue, NW 
  • W Street from Florida Avenue to 9th Street, NW  
  • V Street from 9th Street to 8th Street, NW 
  • 8th Street from V Street to Florida Avenue, NW 
  • Georgia Avenue from V Street to Florida Avenue, NW (access to the hospital) 
  • 5th Street from V Street to Florida Avenue, NW  
  • 4th Street from V Street to Florida Avenue, NW 
  • 3rd Street from Elm Street to Florida Avenue, NW 
  • 2nd Street from Bryant Street to Florida Avenue, NW 
  • Adams Street from 2nd Street to First Street, NW 
  • W Street from 2nd Street to First Street, NW 
  • Elm Street from 5th Street to 2nd Street, NW 
  • V Street from 4th Street to First Street, NW 
  • U Street from 2nd Street to First Street, NW 
  • U Street from 3rd Street to Florida Avenue, NW 
  • Thomas Street from 2nd Street to First Street, NW 
  • T Street from Florida Avenue to First Street, NW 

ይህ የመንገድ መዘጋት ከአሽከርካሪዎች በተጨማሪ የህዝብ ትራንስፖርትን እንደሚያስተጓጉል ፖሊስ አክሎ የገለጸ ሲሆን በተለይም ከዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ ዳውንታውን ዲሲ የሚመላለሱት 70ና 79 ቁጥር ባሶች ከዛሬ ሰኞ ኖቨምበር 4 ምሽት 7pm ጀምሮ የመስመር ለውጥ እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡ ፖሊስ አክሎም ከነዚህ በተጨማሪም ሌሎች የባስና የባቡር አገልግሎቶች በዚህ ጉዳይ ሊስተጓጎሉ ስለሚችሉ ደንበኞች የሜትሮ ባስን የአገልግሎት ድረገጻቸውን በማየት በየጊዜው ያለውን ለውጥ ማየት እንደሚችሉ አስረድቷል፡፡

ከህዝብ ትራንስፖርት በተጨማሪ ለአካል ጉዳተኞችና ለአዛውንቶች አገልግሎት የሚሰጡት የሜትሮ አክሰስ መኪናዎች ፖሊስ በከለከላቸው ቦታዎች ውጪ መደበኛ አገልግሎት እንደሚሰጡና በተከለከሉት ቦታዎች አገልግሎት እንደማይኖር አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም የካፒታል ባይክ ሼር ብስክሌቶች በተለይም በ4th Street and College Street, NWና በGeorgia Avenue and Fairmont Street, NW የሚገኙ የብስክሌት ጣቢያዎች ዝግ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡

የሚዘጉ መንገዶችን ካርታ ዝርዝር ለማየት ይህን ይጫኑ፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት