12/12/2024
Immigration-Temporary Protection

Maribel Hidalgo, 23, of Caracas, Venezuela, stands for a portrait with her son, Daniel, 2, outside a shelter for immigrants in New York, on Wednesday, Nov. 6, 2024. (AP Photo/Cedar Attanasio)

አኒታ ስኖውና ሴዳር አታንሲዮ ለአሶሼትድ ፕሬስ ካዘጋጁት የተወሰደ

ኖቨምበር 14 ኒው ዮርክ

ማሪቤል ሂዳልጎ ከአንድ አመት ልጇጋ በመሆን ተወልዳ ያደገችበትን ቬንዙዌላን ከአንድ አመት በፊት በመልቀቅ በጣም አስቸጋሪ በሆነውና የሰው ልጅ በፍጹም አይዘዋወርበትም የሚባለውን በፓናማ የሚገኘውን የዳሪያን ጋፕ በማቋረጥና በተለያዩ ባቡሮች በመሳፈር ከሜክሲኮ ወደ ደቡባዊ ዩናይትድ ስቴት የገባች ሲሆን ባለፈው አንድ አመትም የባይደን መንግስት ያወጣውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የ17 ሀገራት ዜጎችን የሚያካትተውን የጊዜያዊ ጥበቃና የመኖሪያ ፍቃድ ( TPS) በማመልከት ኑሯቸውን በዩናይትድ ስቴትስ አድርገው ቆይተዋል፡፡

Maribel Hidalgo, 23, an immigrant from Venezuela, pushes a stroller carrying her son, Daniel, 2, outside the Roosevelt Hotel immigration shelter in New York on Wednesday, Nov. 6, 2024. (AP Photo/Cedar Attanasio)

ሆኖም ታዲያ የመጪው አስተዳደር ፕሬዘንደንት ትራምፕና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ የጅምላ ዲፖርቴሽን እንደሚያደርጉ ሲያስታውቁ የቆዩ ሲሆን በተለይም ይህንን ወደ 1 ሚልየን ገደማ ስደተኞችን አቅፎ የያዘውን የጊዜያዊ ጥበቃ ፕሮግራም ( TPS) እንደሚያቋርጡ ሲፎክሩ ከርመዋል፡፡ ምክትል እጩ ፕሬዘደንት ጄዲ ቫንስ በኦክቶበር በአሪዞና ባደረጉት ንግግር ላይ እንዳስቀመጡት ከሆነ በጅምላ ሲሰጥ የነበረው የጊዜያዊ የጥበቃና የመኖሪያና ስራ ፍቃደን እንደሚያስቆሙ ጠቁመዋል፡፡

FILE – Republican presidential nominee former President Donald Trump speaks during a campaign rally at the Gaylord Rockies Resort and Convention Center Friday, Oct. 11, 2024, in Aurora, Colo. (AP Photo/David Zalubowski, File)

ማሪቤል ሂዳልጎ አሁን ሁለት አመት የሆነውን ልጇን እንደያዘች ለጋዜጠኞቹ እንባ እየተናነቃት “ብቸኛው ተስፋዬ ቲፒኤስ ነበር” ያለች ሲሆን አክላም “አሁን ሀሳብ የሆነብኝ እኔና ልጄ እዚህ ለመድረስ ይህን ሁሉ መከራ አይተን እዚህ ከደረስን በኋላ ወደመጣችሁበት ተመለሱ እናባል ይሆን የሚለው ትልቁ ጭንቀቴ ነው” ብላለች፡፡

ቬንዙዌላውያን፤ ሄይቲያውያንና ሳልቫዶርያውያን በቲፒኤስ ተጠቃሚነት ቀዳሚውን ይይዛሉ ተብሏል፡፡

በሄይቲ ከሰሞኑ አገሪቷን እያመሱ የሚገኙት የጋንግ አባላት በአሜሪካ የንግድ አውሮፕላኖች ላይ በተደጋጋሚ ጥይት መተኮሳቸውን ተከትሎ የፌደራል አቪየሽን ባለስልጣን ማንኛውንም የንግድ በረራ ለ30 ቀን አቋርጧል፡፡ ይህም ሌላ ጭንቀት እንደሆነና በተለይም በሺዎች ለሚቆጠሩ ለሄይቲ ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ የማይታሰብ እንደሆነ የሄይሺያን ታይምዝ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ቫኒያ አንድሬ ተናግረዋል፡፡

FILE – A man shows bullet casings he collected from the streets near his home days after an armed gang attack on Pont-Sonde, Haiti, Tuesday, Oct. 8, 2024. (AP Photo/Odelyn Joseph, File)

በሆምላንድ ሴኪውሪቲ የተደነገገው የቲፒኤስ ድንገጋ እስከ 18 ወር የሚቆይ ሲሆን ከዚህ ቀደም በነበረው ኝ እንደ ሀገራቱ ሁኔታ ይራዘም ነበር፡፡ የኤልሳልቫዶር ቲፒኤስ በማርች 2025 የሚያበቃ ሲሆን የሱዳን ዩክሬይንና ቬንዙዌላ ደሞ በኤፕሪል 2025 ያበቃል፡፡ የኢትዮጵያ ቲፒኤስ እስከ ዲሴምበር 2025 ይቀጥላል፡፡

ከዚህ ቀደም የትራምፕ አስተዳደር የበርካታ አገራት ዜጎች ቲፒኤስ እንዳይታደስና ኤክስፓየር እንዲይደርግ የሞከረ ሲሆን ፍርድ ቤቶች ይህንን ሲከላከሉ ቆይተው ነበር፡፡ ይህንን የትራምፕ እርምጃ ከተቃወሙትና ወደፍርድ ቤት በመውሰድ የተገዳደሩትና  በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ ስኩል ኦፍ ሎው አስተማሪ የሆኑት ጠበቃ አይላን አሩላንታም ፕሬዘንደት ትራምፕ አሁንም ይህንን ከማረግ ወደኋላ እንደማይሉ ተናግረዋል፡፡

ጠበቃው አክለውም “በአስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ጥቂት ሰዎች የሚልየኖችን የስራ ፍቃድ በማገዳቸው በተለይም አንዳንዶች ለአስርት አመታት እዚህ አገር መኖራቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር እንደሚከተልና በጎ ፖሊሲ እንዳልሆነ የሚገነዘቡ ይመስለኛል” ያሉ ሲሆን ፕሬዘደንት ትራምፕ ግን በታሪካቸው ለእንዲህ ያለ ጉዳይ የተጨነቁበት ጌዜ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *