ምስል: ከሜትሮ ትራንዚት ፖሊስ
የሜትሮ ፖሊስ ከሰሞኑ የወጣውን ህግ ለማስከበር ደንብ አስከባሪ ፖሊሶችን በዩኒፎርምና በሲቪሊያን ልብስ ተሳፋሪዎች የባስ ሂሳባቸውን መክፈላቸውን ለማረጋገጥ እየላከ ይገኛል:: ታዲያ በX2 ባስ ላይ ይህን ደንብ ለማስከበር ተሳፍረው የሚጏዙ ሁለት ሲቪል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች አንድ ተሳፋሪ ሳይከፍል ሊሳፈር ሲሞክር ይይዙትና እንዲከፍል ሲጠይቁት አሻፈረኝ ይላል:: ይህን ተከትሎም በቁጥጥር ስር አውለው ሲፈትሹት ከስር በምስሉ የምትመለከቱትን ጠመንጃ በጃኬቱ ስር ተደብቆ ተገኝቷል:: ተጠርጣሪውም ወደ ዘብጥያ ወርዷል:: ምን አይነት ክስ እንደሚመሰረትበት እስካሁን የተባለ ነገር የለም::