የሞንጎምሪ ካውንቲ መንግስት ያዘጋጀውና በርካታ የምንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተሳተፉበት የሪሶርስ ፌይር ላይ የኢትዮጲክ ባልደረቦች እድል አግኝተው የካውንቲው ካውንስል ፕሬዘደንት የሆኑትን ኬት ስቴዋርትንና የካውንቲውን ኤክስኪውቲቭ ማርክ ኤልሪችን አናግረው የሚከተለውን ይዘው ቀርበዋል። በዚህ አውደርዕይ ላይ የካውንቲው መንግስት ለነዋሪው ያለውን ቁርጠኛነትና በዋይት ሀውስ የትኛውም መንግስት ቢገባ ለነዋሪዎቻቸው ይሰጡ የነበሩት አገልግሎቶች ሳይቋረጡ እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል። ኢትዮጲክ ላለፉት 2 አመታት የነበሩትን የካውንስል ፕሬዘደንቶች ስትወተውት ከነበረችበት ጉዳይ አንዱ የሆነውን የቋንቋ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት ታዲያ የካውንቲው ካውንስል ፕሬዘደንት ሆነው የተሾሙት ኬት ስቴዋርትም በካውንቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት የዜና መጽሄታቸውን በአማርኛ እያዘጋጁ እንደሆነ ጠቁመዋል። እኚህንና ሌሎች ጉዳዮችን ከቪዲዮው ይከታተሉ።