12/11/2024
465787706_554609503990083_705646106192066180_n

ባለሞያዎች እንደሚሉት ከሆነ በዚህ ወቅት ወዳጃችሁ ፍርሀት ሳይሆን ዝግጅት ነው። በአካባቢዎ ያሉ መረጃዎችንና ጠቃሚ መርጃዎችን እነሆ። 

ይህ መጣጥፍ በ The 51st, ኢትዮጲክ-Ethiopique, and El Tiempo Latino. በጋራ ተዘጋጅቷል። 

“Un Pueblo Sin Murales Es Un Pueblo Desmuralizado / A People Without Murals is a Demuralized People” is the oldest mural created by Latino artists in the District. A plaque next to it reads “Dedicado a todos aquellos que lucharon por hacer y mantener esta vecindad su hogar. / Dedicated to all those who struggled to make and keep this neighborhood their home.” (Eric Falquero)

ፕሬዘደንት ትራምፕ ከስደተኞችጋ በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ ጸረ-ስደተኛና ዘረኝኝነት የሚታይባቸው ከሀቅ የራቁና አሳሳች  ንግግሮችን በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ሲያደርጉ ተደምጠዋል። በየጊዜውም የሚጠቀሙት ቋንቋና የሚያቀርቧቸው የፖሊሲ አማራጮች ጽንፍ እየረገጡ ከመሄዳቸውም በላይ ስደተኞችን በተለይም በውስጣችን የተሰገሰጉ ጠላት ብለው የፈረጇቸውን በጅምላ ከአገር እንደሚያባርሩ ሲፎክሩ ከርመዋል።  

የትራምፕ የስደተኞች ፖሊሲ እስካሁን ግልፅ አይደለም፤ ያናገርናቸው ባለሞያዎችም ፕሬዘደንቱ ምን ይዘው ይመጣሉ የሚለውን ለመተንበይ ወይንም ለማወቅ ጊዜው ገና እንደሆነ ጠቁመዋል። አልፎ ተርፎም ፕሬዘደንቱ ይዘዋቸው የሚመጧቸው አዳዲስ ህጎችና ፕሬዘደንታዊ ህጎች በፍርድ ቤት ተቃውሞ ሊገጥማቸው እንደሚችል ይጠበቃል።  

ሆኖም አንዳንድ ዝርዝር ጉዳዮች አሁን መገለፅ ጀምረዋል፡ ለምሳሌ እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ የጅምላ አፈሳና ማባረር እቅዳቸውን ለማሳካት እንዲሁም እስካሁን ተግባራዊ እየተደረገ የነበረውን በድንበር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞችን ይዞ መልቀቅ ለማስቀረት መጪው ፕሬዘንደት የማጎሪያ ጣቢያዎችን ማስፋፋት እንዳቀዱ ተነግሯል።  ትራምፕ በተጨማሪም ቆሞ የነበረውን ስደተኞች በሜክሲኮ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚያስገድደውንና “remain in Mexico” የተባለውን ህግ ወደስራ ሊመልሱት እንደሚችሉ ይጠረጠራል። (የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ካውንስል ይህ አካሄድ በረጅም ጊዜ አሜሪካንን ከግማሽ ትሪሊየን ዶላር በላይ ያስወጣታል ሲል ግምቱን በማስቀመጥ ይህም የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚጎዳው ጠቅሰዋል።  

ለ51st ሀሳባቸውን ያካፈሉ የህግ ባለሞያዎች በፕሬዘደንት ትራምፕና በባልደረቦቻቸው (በፀረ-ስደተኛ አቋሙ የሚታወቀው ስቴፈን ሚለርን ጨምሮ)፣ በሚያቀርቧቸው  ሀሳቦችና ፖሊሲዎች   ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸውን ሰዎች ላይ በርካታ ምርመራዎች፤ በአሳይለም ጉዳያቸውን የሚከታተሉ ሰዎችን ወደ ማባረር እንዲሁም በጊዜያዊ ጥበቃ ስር (TPS) ያሉ ሰዎችንም ህጉን ለማስቀረት ሊሞክሩ ይችላሉሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።  

ፕሬዘደንት ትራምፕ በመጀመሪያው የፕሬዘደንትነት ዘመናቸው ካደረጓቸው 472 ከስደተኞችጋ የተገናኙ ድርጊቶቻቸው በዋናነት ያተኮሩት የጊዜያዊ ጥበቃን (TPS) መንፈግና አሳይለም (ጥገኝነትን) መከልከል ላይ ያተኮሩ ነበሩ። እስከ መስከረም 2024 ድረስ በዋሽንግተን ዲሲ ከ2,860 ያህል ሰዎችን በጊዜያዊ ጥበቃ (TPS) ስር የነበሩ ሲሆን ከዚህም ውስጥ አብዛኛው የኢትዮጵያና የኤልሳልቫዶር ዜጎች ይገኙበታል።  

በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጡን የጠይቅናቸው የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ቢሮ ጥያቄያችንን ውድቅ በማድረግ የምርጫው ውጤት በተገለጸበት ወቅት ከንቲባዋ የሰጡትን ፕሬስ ኮንፍረንስ እንድናጣቅስ መርተውናል።  

በዚህ ፕሬስ ኮንፍረንስ  ላይም ከንቲባዋ “ምንም እንኳ ፕሬዘደንቱ በምን አይነት መንገድ የስደተኛ ፖሊሲዎቹን እንደሚያስፈጽም መቆጣጠር ባንችልም፤ ለብዙ አመታት እዚህ ለኖሩት ነዋሪዎች ድምጽ ልንሆናቸው ይገባል።” ከንቲባዋ አክለውም “በከተማችን በጊዜያዊ ጥበቃ ስር (TPS [Temporary Protected Status] ያሉ ነዋሪዎቻችንን እንፈልጋቸዋለን። በሂደትም ዜጋ የሚሆኑበት መንገድ መኖር እንዳለበት እናስባለን” ብለዋል።  

በዲሲ አካባቢ ብቸኛው የአማርኛ አካባቢያዊ ዜናዎች አገልግሎት ሰጪ የሆነችው ኢትዮጲክ ለአንባቢዎቿ ባቀረበሽው መጠይቅ 95%ያህሉ ስለመጪው ጊዜ ሲያስቡ እንደሚሰጉ አስታውቀዋል። በዚህ መጠይቅ እኚሁ አንባቢዎች ከ55 በላይ ጥያቄዎችን ለኢትዮጲክ የላኩ ሲሆን  እኚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ከመለሰ በሚል እንዲሁም ለስደተኞች እንደ አጋዥ የሚሆን አንድ ወጥ መርጃና የህግ ባለሞያዎች ማውጫ የዚህ መጣጥፍ አዘጋጆች የሆኑት The 51st, ኢትዮጲክ-Ethiopique, and El Tiempo Latino. አዘጋጅተዋል።  

የሌጋል ኤይድ ዲሲ የስደተኞች ህግ አገልግሎትን የምሚቆጣጠሩት ዲፓ ቢጅፑሪያ እንዲህ ሲሉ መክረዋል “የኔ ምክር የሚሆነው በአስቸኳይ ሳይዘገዩ የህግ ምክር እንዲያገኙ ነው። ሰዎች ጥርት ያለ መልስ ይፈልጋሉ .. ሆኖም ማንኛችንም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለማናውቅ፤ በኋላ ሊጠቅሙን የሚችሉና ቀድመን መዘጋጀት ያሉብን ነገሮች ይኖራሉ።” 

የዋርድ 4 ካውንስል አባል ጃኒስ ሊዊስ ጆርጅ ከሰነድ አልባ ነዋሪዎችጋ በመሆን ኤፕሪል 15 “የስደተኞች የጽናት ቀን” ተብሎ እንዲታወስ በ2021 ወስነዋል። (ምስል፡ United We Dream)) 

Note: We’re not lawyers and this is not legal advice. But we talked to local attorneys, service providers, and officials to distill steps any residents without full U.S. citizenship can take if they are worried about their immigration status. 
ማስታወሻ፡ እኛ የህግ ባለሞያዎች አይደለንም ። ይህም የህግ ምክር አይደለም። ሆኖም በርካታ የህግ ባለሞያዎችን፤ አገልግሎት ሰጪዎችንና ባለስልጣናትን አናግረንና ከነሱ ያገኘነውን መረጃ በተለየም የአሜሪካ ዜጋ ላልሆኑና በዚህም ሀሳብ የገባቸው ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚችሏቸውን እርምጃዎች ነው ያጠናቀርነው። 

  1. የደህንነት ዕቅድ ያውጡ 

ማንኝውም ጉዳዩ የሚያሳስበው ስደተኛ የሚከተሉትን ጠቅላላ አማራጮችን ማሰብ ይኖርበታል። “ሰዎችን ማስፈራራት አልፈልግም ግን በግምት አለም ውስጥም መኖር አልፈልግም” ያሉት ቢጅፑሪያ በተለይም በአንድ ቤት ውስጥ የተለያየ የስደተኛ ኬዝ ካላቸው ለምሳሌ አንዱ የቤተሰብ አባል ህጋዊ ሆኖ ሌላው ካልሆነ የሚከተሉትን ማድረግ ይመከራል፡ 

  • የኢሚግሬሽን ጠበቃ ያናግሩ፡ ጥበቃዎች (የህግ ባለሞያዎች) ሌላ ህጋዊ መሆን የሚቻሉባቸው መንገዶች ካሉ ይጠቁሟችኋል። (የህግ ባለሞያዎችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ በተራ ቁጥር 3 ላይ ተቀምጧል።  
  • የጠበቃዎትን ቢዝነስ ካርድ ወይንም መረጃ ሁሌም መያዝዎትን አይርሱ። 
  • መታወቂያዎትንና ሌሎች አስረጅ ወረቀቶች ሁሌም ይያዙ፡ ግሪን ካርድ ካሎት ሁሌም ይዘውት ይሂዱ፤ በህጉ መሰረት ሁሌም ሊይዙት ይገባል የአሳይለም ጉዳይዎትን እየተጠባበቁ ከሆነ የማመልከቻዎ ቁጥር ያለበትንና ያመለከቱበትን ማስረጃ ደረሰኝ ይያዙ።  
  • ለሚያምኑት ሰው ህጋዊ ውክልና ይስጡ (legal power of attorney (POA)፡ እንደ አሜሪካን ኢሚግሬሽን ካውንስል ከሆነ ብዙውን ጊዜ በኢሚግሬሽን ተቆጣጣሪዎች የተያዙ ሰዎች ንብረቶች ይጠፋሉ፤ ይበላሻሉ ወይም ይሰረቃሉ። ሆኖም ህጋዊ ውክል የተሰጠው ሰው ካለ ግን ያ ሰው ንብረትዎንና ገንዘብዎን ሊጠብቅልዎት ይችላል። እርስዎ ቢያዙ ቢታሰሩ ወይም ቢባረሩ ሀብት ንብረትዎ በወኪልዎ በኩል ደህንነቱ ተጠብቆ መቆየት ይችላል። ይህ ውክልና የተሰጠው ሰው ሀብት ንብረትዎን ሊያጠፋው ወይም ሊክድዎት ስለሚችል ለሚያምኑት ሰው ብቻ ይስጡ።  
  • ለልጆችዎ ህጋዊ ሞግዚት ማን እንደሚሆን ያዘጋጁ፡ በዲሲ “የተጠንቀቅ ሞግዚት” ፕሮግራም ወላጆች ቢሞቱ ወይንም ቢታሰሩ ልጆች አሳዳጊ እንዲያገኝ የሚችሉበት ፕሮግራም ሲሆን ወላጆችም ወላጅነታቸውን በዘላቂነት እንደተጠበቀ ይቆያል።  
  • እቅድዎትንን በፅሁፍ ያስቀምጡ፡ ዩናይትድ ዊ ድሪም የተባለው ተቋም ለዚህ ጊዜ ያዘጋጁትን ፕላን ወይም እቅድ በአንድ ፎልደር ምስጢራዊ ብለው በማዘጋጀት ለሚታመን ሰው እንዲሰጡ ይመክራል 

የዲሲ ህጻናትና ቤተሰብ አገልግሎት ቢሮ የተጠንቀቅ ሞግዚትን የሚያብራራና እንዴት ይህን አገልግሎት መጠቀም እንደሚቻል የሚያብራራ መመሪያ በእንግሊዝኛና በስፓኒሽ አዘጋጅቷል።  በተጨማሪም የሚከተሉትን ሰዎችጋ በመደወል የጽሁፍ ወይም የቃል የትርጉም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል። Grenetta Wells (202) 321-0062 or Christina White (202) 497-4387 


የኢሚግራንት ሎው ሴንተርም እንዲሁ ስደተኞች እቅዳቸውን የሚያሰፍሩበትና የሚያዘጋጁበት መርጃ በእንግሊዝኛና ስፓኒሽኛ አዘጋጅቷል።  

  1. መብትዎን ይወቁ  

በጎዳና ወይንም በመኖርያ ቤትዎ ከተጠየቁ በራስ መተማመንዎን ሳያጡ መብትዎን ማስከበር እንዲችሉ ምን አይነት መብቶች እንዳለዎት ይወቁ።  

አገር አቀፍ የመብት ተከራካሪ የሆኑት አሜሪካን ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን ((ACLU)ዩናይትድ ዊ ድሪም ሰዎች በተለያየ ሁኔታ  የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች በተለይም ከህግ አስከባሪዎችጋ በተያያዘ የሚኖራቸው ን የመስተጋብር አማራጭ በዝርዝር የሚዳስስ መድብል አዘጋጅተዋል።  

የዩኤስ ኮሚቴ ፎር ሬፊውጂስ ኤንድ ኢሚግራንትስ በበኩሉ ታትመው በኪስ ተይዘው መዞር የሚችሉ ካርዶች አዘጋጅቷል። በነዚህ ካርዶችና መርጃ መድብሎች ላይ ካሉት ወሳኝ መረጃውች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡ 

  • ህግ አስከባሪ ካስቆመዎት ምንም ያለመናገር መብት አለዎት። (በአሪዞና፤ ፍሎሪዳ፤ ኢንዲያና፤ ሉዊዚያና፤ ኔው ሜክሲኮ፤ ኦሀዮና ቬርሞንትን በመሳሰሉ ስቴቶች ስምዎትን መናገር ግዴታ ነው።) 
  • ለመናገር ከወሰኑ ደሞ በፍጹም ስለ ኬዝዎ እንዳይዋሹ – ማንኛውም ንግግርዎት እንደማስረጃ ሊያዝና እርስዎን የሚጎዳ ሊሆን ይችላል።  
  • የኢሚግሬሽን ፖሊስ ወይንም ሰራተኛ ወረቀቶችዎን ለማየት ከጠየቀ ና በወቅቱ እጅዎት ላይ ካለ መስጠት ግዴታዎ ነው።  
  • በአብዛኛው ጉዳያቸው እየታየላቸው ያሉ ስደተኞች ለእስር ከተደራጉ በዋስ ወይንም በሌላ መንገድ ለመውጣት ብቁ ናቸው።  
  • ከታሰሩ ጠበቃዎጋ ወይንም ቤተሰብጋ ስልክ የመደወል መብት አለዎት እንዲሁም በታሰሩበት ቦታ በጠበቃዎ የመጎብኘት መብትዎ የተጠበቀ ነው።  
  • የኢሚግሬሽን ዳኛጋ ከቀረቡ ጠበቃዎ አብሮዎት የመገኘት መብት አለዎት።  

የዲሲ ኤ.ሲ.ኤል.ዩ መብትዎን ይወቁ የሚል ስልጠና ለሚፈልጉ ሰዎች በነጻ ይሰጣል። እርስዎም ይህን ስልጠና መውሰድ ከፈለጉ በሊንኩ ተመዝግበው ስልጠናውን መውሰድ ይችላሉ።  


የዲሲ በጎ ፍቃደኛ ጠበቃዎች ና የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ቢሮ የየራሳቸውን መብትዎን ይወቁ የሚሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ቪዲዮዎች አሏቸው። በተጨማሪም የጽሁፍና የቪዲዮ ተመሳሳይ መረጃዎች ከዲሲ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ። 

 

  1. የህግ ባለሞያ (ጠበቃ) ያናግሩ 

የአገሪቱ የስደተኞች ህግና የህጉ አተገባበር በጣም ውስብስብ በመሆኑ ምክንያት የአንዱ ሰው ጉዳይ ከሌላው ፍጹም እንዲለያይ ያደርገዋል። አንዱ ገና በእንጥልጥል ያለ ጉዳዩ ሲያሳስበው ሌላው ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃዴን አጣ ይሆን ብሎ ይጨነቃል።  

“አንድ ሰው የኢሚግሬሽን ጠበቃ ከሌለው ጉዳዩ ውስብስብ ይሆንበታል። በተለይም ጉዳይዎት ታይቶ ከአገር እንዲወጡ ከተወሰነበዎት የበለጠ ከባድ ቢሆንም በዛ ደረ ጃላይ ባይሆኑም እንኳን ከባድ ነው።” ይላሉ የህግ ባለሞያው ቢጅፑሪያ። እንደ ባለሞያው ከወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ቀጥሎ የስደተኞች ህግ በሰዎች ህይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው ጠቁመው “አንድ ሰው ራሱን ወክሎ ተከራክሮ የማሸነፍ እድሉ ጠባብ ነው።” ይላሉ። ከስር በምስሉ እንደሚታየው በጠበቃ ከተወከሉ ኢትዮጵያውያን አሳይለም ጠያቂዎች 12% ገደማ የሚሆኑት የተከለከሉ ሲሆን ያለጠበቃ በራሳቸው ከቀረቡት ግን ከ65% በላይ ተከልክለዋል።  

ከ2012 እስከ 2017 አሳይለም የተከለከሉ ሰዎች ቁጥር በጠበቃ የተወከሉና ራሳቸውን ወክለው የሄዱ ማነጻጸሪያ። ቀይ- በጠበቃ የተወከሉ ቢጫ-በራሳቸው ብቻቸውን የቀረቡ (Transactional Records Access Clearinghouse) 

አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች፤ በርከት ያሉ በአካባቢያችን ያሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የነጻ ወይንም በአነስተኛ ክፍያ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣሉ። 

ጥቂት ድርጅቶች ደሞ ማንኛውም ሰው ያለቀጠሮ ጉዳዩን ይዞ በመሄድ መገልገል የሚችልባቸውን አጋጣሚዎች አመቻችተዋል። ለምሳሌም፡ 

የዲሲ ሌጋል ኤይድ በ2041 Martin Luther King Jr . Ave. SE Suite 201 ቅርንጫፉ በየሳምንቱ ሰኞና ሀሙስ ከጧት 10፡00 a.m. እስከ ከሰዓት 2:30 p.m. ማንኛውም ሰው ጉዳዩን ይዞ ሄዶ የህግ ምክር አገልግሎት ማግኘት ይችላል። በ1331 H St. NW, Suite 350. ደሞ ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ ከ12:30pm እስከ 4፡00pm በተመሳሳይ መስተናገድ ይችላል። በተመሳሳይም ከሰኞ እስከ ረቡዕ ከጧት 10am እስከ 3pm በስልክ ቁጥር 202-628-1161 በመደወል ወይንም በዚህ ሊንክ በመመዝገብ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።  


የአፍሪካን ኮሚውኒቲስ ቱጌዘር የዲሲ ቅርንጫፍ ነጻ የህግ ምክር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ራሳውቸን ወክለው መቅረብ ለመረጡ ሰዎችም ሁሌ ረቡዕ ከጧት 10am እስከ 1pm በ700 Pennsylvania Ave. SE, 2nd Floor. የማማከር አገልግሎት ይሰጣል። በተጨማሪም በአካል የሚዘጋጁ የማማከር አገልግሎቶች በቡድን ሆነው ለሚመጡ የሚያቀርቡ ሲሆን ይህን አገልግሎት ለማግኘት በኢሜይል DMV@africans.us ወይንም በስልክ 202-816-0416 ለዲሲና በ240-621-0194 ለሜሪላንድ በመደወል ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል። 

ሌችሎ አብዛኞቹ ተቋማት ደንበኞች አስቀድመው ስልክ እንዲደውሉና ቀጠሮ እንዲያሲዙ ይጠብቃሉ የተወሰኑት ደሞ ከ100 ዶላር ያልበለጠ የአገልግሎት ክፍያ ይጠይቃሉ።  

ስለነዚህ ድርጅቶችና አገልግሎቶቻቸው ለማየት ከስር ያሉትን ይመልከቱ 

የዲሲ ሌጋል ኤይድ በአካባቢው ያሉ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትንና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን በእንግዚዝኛ አዘጋጅቷል። ይህ ዝርዝር የትኞቹ ገንዘብ እንደሚያስከፍሉ የትኞቹ ደሞ የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል እንደሚያገለግሉ በዝርዝር አስቀምጧል።  


ሌላው በጣም ጠቃሚ የሆነ የኢሚግንራት አድቮኬት ኔትወርክ የተባለው በውስጡ በመላው አሜሪካ የሚገኙና ካስፈለገ በዚፕኮድ መፈለግ የሚያስችል ከስደተኞችጋ የሚሰሩ ተቋማትን ዝርዝር መረጃ የያዘ የመረጃ ቋት ነው። ይህ መረጃ በ12 ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን የአማርኛ አገልግሎት ግን የለውም።  

ከላይ የተጠቀሱት ተቋማት አልፎ አልፎ ማንኛውም ሰው ያለ ቀጠሮ በአካል ሄዶ የሚስተናገድበት ፕሮግራሞችን ያዘጋጃሉ። ድረ-ገጻቸውን በመጎብኘት፤ የፕሮግራም ካላንደራቸውን በማየት ወይንም በኢሜይል በመመዝገብ በየጊዜው ያላቸውን ፕሮግምራም መከታተል ይቻላል። 

የዲሲ ባር የነጻ (በጎ ፍቃድ) አገልግሎት የህግ ምክር አገልግሎት ለዲሴምበር 7 አዘጋጅቷል። 


የዲሲ ባር በተጨማሪም አውቶሜትድ የችግር ጊዜ መርጃ የስልክ አገልግሎት አለው። በዚህ አገልግሎት ደንበኞች ለጥያቄዎቻቸው መሰረታዊ መልሶችን ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም የህግ ባለሞያዎችን መገኛና የመሳሰሉ ጠቃሚ መረጃዎችን በአማርኛ፤ በእንግሊዝኛ፤ በፈረንሳይኛና በስፓኒሽየ24 ሰዓት አገልግሎት ለማንኛውም ሰው ያቀርባል። ይህን አገልግሎት በስልክ ቁጥራቸው 202-626-3499 በመደወል ማግኘት ይቻላል።  

ያለውን ፍላጎት የሚያሟላ የኢሚግሬሽን ጠበቆች እንደልብ አይገኝም እናም አእገልግሎት ፈላጊዎች ሳያሰልሱ እነዚህ ተቋማትጋ መደወል ይኖርባቸልዋ። ደውለው የድምጽ መልዕክት ካስቀመጡ በኋላ መልሰው ካልደወሉልዎ በድጋሚ ይደውሉላቸው። በዚህ ሳምንት ቀጠሮ ቦ ታየለም ከተባሉ በመጪው ሳምንት ይደውሉ። ምንም እንኳ ሰዎቹ እርስዎን ለመርዳት ፈቃደኛ ቢሆኑ፤ ያሉት ድጋፎች ውስን ናቸው።  

የህግ ባለሞያው ቢጅፑሪያ “መፍራትና መደንገጥ ቀላል ነው ግን ሁላችንም እንረዳዳለን። ጥልቅ ትንፋሽ በመውሰድ ራስን ማረጋጋት ያስፈልጋል።” ብለዋል። ባለሞያው አክለውም “በአካባቢያችን ያሉ ሁሉም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ተሰብስበው ምን ማድረግ እንደሚችሉ ሲማከሩ ቆይተዋል። ሁሉም ሰው በአንድነት የሰዎችን መብት እንዲጠበቅ ለመጠየቅ የሰባሰባል የሚል ተስፋ አለኝ።” ሲሉ አክለዋል።  

ሁሉም ተቋማት ሁሉንም ሰው አያስተናግዱም አንዳንዶቹ መርጠው የተወሰነው ተጎጂ ብቻ ነው የሚያገለግሉት ለምሳሌ፡ 

ዘ አሚካ ሴንተር ፎር ኢሚግራንት ራይትስ ለይቶ በፖሊስ የታሰሩ ስደተኞችን ብቻ ነው የሚያገለግለው። የታሳሪ ወዳጅ ዘመዶች ይህንን ሊንክ በመጫን ድጋፍ መጠየቅ ይችላሉ።  


የኤሽያ ፓሲፊክ አሜሪካን ሌጋል ሪሶርስ ሴንተር በስልክ ቁጥራቸው በ202-393-3572 በቻይኒኛ፤ በሂንዲ፤ በኮሪያኛ፤ በቬትናም እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የድጋፍ አገልግሎት ይሰጣሉ። ድረ-ገጻቸውም በበርካታ ቋንቋዎች መረጃዎችን ያቀርባል። 

የገቢ መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑና የነጻ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቁ የሆኑ ሰዎች በአብዛኛው ጠበቃ ለመቅጠር ሲቸገሩ ይስተዋላል። ባለሞያዎች ታዲያ በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችሉ ከሆነ በወርሀዊ ክፍያ መክፈል የሚችሉበት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ (payment plan) በመጠየቅ ሸክማቸውን በከፊል ማቅለል ይችላሉ።  

የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ሎውየርስ አሶሴሽን የህግ አገልግሎት ማግኘት የሚሹ ሰዎች ከጠበቆችጋ እንዲገናኙ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ሲሆን በዲሲ የሚገኘው የማህበሩ ቅርንጫፍ በርካታ ስራዎችን የሚሰራ ቅርንጫፋቸው ነው። 

ለዚሁ ጽሁፍ ያናገርናቸው የማይግራንት ሶሊዳሪቲ ሙቹዋል ኤይድ ውስጥ በበጎ ፈቃደኛነት የሚያገለግሉት ኤሚ ፊሸር “ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ጠበቃ የማግኘት መብት አለው። ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት ነው። ይህ መብት ግን ለኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት አይሰራም። ይህን ተከትሎም በርካታ ስደተኝኖች ጉዳያቸውን የሚከታተሉት ያለ ባለሞያ ድጋፍና እርዳታ ነው። ባለፉት አመታት አዚህ አገር የመጡ በርካታ ስደተኞች ያለ ምንም የህግ ድጋፍ ነው ፍርድ ቤት የሚከራከሩት።”  

ለነዚህ ሰዎች ታዲያ በህይወታቸው ላይ መጥፎ ውጤት ያመጣል። ባለሞያው ቢጅፑሪያ ሲናገሩ “ልክ እንደ ወንጀል ህጉ የስደተኞች ህግና ውጤቱ ቤተሰቦችን የሚለያይ ሲሆን ለበርካታ ሰዎች ወደ አገራቸው ሲመለሱ ሞት ሊጠብቃቸው ይችላል።” ሲሉ አስረድተዋል።  

  1. የሚያናግሩት የህግ ባለሞያ በእርግጥ ባለሞያ ነው? 

የኢሚግሬሽን ጉዳይ የትምህርት ብቃቱና እውቀቱ በሌላቸው አስመሳዮች የተሞላ ነው። ባለሞያው ቢጅፑሪያ እንደሚሉት “የኢሚግሬሽን ጠበቆች በየጊዜ ባለሞያ ባልሆኑ አጭበርባሪዎች የተሸወዱ ሰዎችን ያስተናግዳሉ። ባለሞያ የሆኑና ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ሰዎችም እንዲሁ ያልተገባ ነገር ሲያደርጉ ይስተዋላል። ለጠቅላላው ግን ‘notario fraud.’ ብለው ጉግል ቢያደርጉ በተለይ በኢሚግሬሽን ዙሪያ ያሉ ማጭበርበሮችን ማየት ይችላሉ።” ባለሞያው አክለውም “ያለ ፍቃድ የህግ ሙያ አገልግሎት መስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ በወንጀል ያስጠይቃል። ነገር ግን ቲክ ቶክ ላይ ስትሄድ ሰዎች ያንተን የኢሚግሬሽን ሽግር እንደሚፈቱልህ ሲምሉና ሲገዘቱ አልፎ አልፎም እስከ $5000 ክፍያ ሲጠይቁ ታያለህ። ይህ በጣም መጥፎ ድርጊት ነው።” 

የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችና ስደተኞች አገልግሎትም በዚሁ ጉዳይ ሰዎች ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ ያሳስባል። 

እንዲህ ባሉ አጭበርባሪዎች ሰለባ የሆነ ወዳጅ ዘመድ ካለዎት አዩዳ የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በአካባቢያችን ያሉ ስደተኞች በቋንቋ ችግር፤ በባህል ልዩነትና በገንዘብ አጠቃቀም ያለውን ልዩነት ተጠቅመው የሚያጭበረብሩ ለመከላከል እንዲሁም ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ለማድረግ “ሮጀክት ኢንድ የተባለ ፕሮግራም አለው።

እና እንዴት ነው ጥሩውን ከመጥፎ ትክክለኛውን ከአጭበርባሪ የሚለዩት? በቀላሉ የጠበቃዎን ማንነት በኢንተርኔት በመፈለግ ማጣራት ይችላሉ። ዘለቅ ያለ ምርመራ ለማድረግ ደሞ፡  

ጠበቃዎን “የባር ቁጥራቸውን” (“bar number”) በመጠየቅና በየትኛው ስቴት ለመስራት ፍቃድ እንዳላቸው በመጠየቅ ይህንን መረጃ ይዘው እንደ ስቴቱ የባር ድረ-ገጽ ላይ በመሄድ እውነትም ይህ ባለሞያ ፍቃድ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል። ለምሳሌ የዲሲ ባ፤ ወይንም  የሜሪላንድ ባር ወይንም የቨርጂንያን ስቴት ባር ሊንኮቹን በመከተልና መረጃዎቹን በማስገባት አንድ ሰው በትክክል የህግ ባለሞያ እንደሆነና እንዳልሆነ ማጣራት ይችላሉ።

  1. ከማህበረሰብ አካላትና ማህበራትጋ በየጊዜው ይገናኙ  

ለማንኛውም ሰው በዙሪያው ያለ ማህበረሰብ ወሳኝ ነው። የዚህ ማህበረሰብ አባላትም ከመንግስት አካላት ወይም ከተቋማት በተሻለ የገንዘብና የቁስ ድጋፍ ከማድረግ አልፈው የመንፈስ ድጋፍም ስለሚያደርጉ ጥቅማቸው የጎላ ነው። ለዚህ ምሳሌ የሜኒ ላንጉዌጅስ ዋን ቮይስ የተሰኘ የስደተኛ ማህበረሰቦችንና ድጋፍ ሰጪ ተቋማትን የሚያደራጅ ተቋም ሲሆን በተለይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ውስንንነት ያለባቸውን ሰዎች በማህበረሰባዊ ጉዳዮች እንዲሳተፉ ትልቅ ሚና ይጫወታል።  

በተለይም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ የተቋቋሙ ሙቹዋል ኤይድ (mutual aid”) የተባሉ በርካታ እድር መሳይ አደረጃጀቶችም ጎረቤቶችን በማሰባሰብና ለአንድ አላማ በማሰለፍ በርካታ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። 

ባሳለፍነው ወር ታዲያ የ The 51st አዘጋጆች በከተማው ያሉ የሙቹዋል ኤይድ አደረጃጀቶችንና ተመሳሳይ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ዝርዝር አጠናቅሯል።  


በተለይም ለስደተኞች ተብሎ የተቋቋመው የማይግራንት ሶሊዳሪቲ ሙቹዋል ኤይድ የተባለው አደረጃጀት እንደ ምግብ አቅርቦት፤ የህግ ማማከር፤ ማመልከቻዎችን ማዘጋጀትና አልባሳትን በነጻ ማቅረብ የመሳሰሉ ሁሉን አቀፍና ሰብዓዊ  አገልግሎቶችን ያቀርባል።  

ይህ አደረጃጀት በዋናነት በመጀመሪያው የትራምፕ አስተዳደር ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስመንት (አይ.ሲ.ኢ) ይደረጉ የነበሩ ድንገተኛ ፍተሻዎችንና አፈሳዎችን ለመቃወም ከተቋቋመውና ሶሊዳሪቲ ዲ ኤም ቪ ከተባለው ማህበር የወጣ አደረጃጀት ነው። በ2022 የቴክሳሱ ገቨርነር አቦት ስደተኞችን በባስ ጭነው ወደ ዲሲ በላኳቸው ጊዜም ይህ ተቋም ከሌሎች ተመሳሳይ አላማን ካነገቡ ተቋማትና ግለሰቦችጋ በመሆን ለስደተኞቹ ድጋፍ አድርገዋ ነበር። 

ከቴክሳስና አሪዞና የሚመጡ ስደተኞችን ለማገዝ የዲሲ መንግስት የስደተኞችን ጉዳይ የሚመለከትና ድጋፍ የሚያደርግ ቢሮ የከፈተ ሲሆን የስትሪት ሴንስ ሚዲያ ከዚህ ቀደም በሰራው ዘገባ የዲሲ ሰብዓዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት አገልግሎቱን የሚጠቀም ሰው በብዛት ባለመኖሩ አገልግሎቱን ሊቀንስ እንደሆነ ተጠቁሞ ነበር። ይህ የመስተናገጃ ቢሮ በጁን 2024 የተከፈተ ሲሆን እስከ ኖቨምበር 20 ባለው ጊዜ 5000 ስደተኞችን እንዳስተናገደ ተነግሯል።  

ቢሮውን ለማናገር ወይንም አገልግሎት ለመጠየቅ የተሻለ የተባለው በኢሜይል migrant.services@dc.gov. ሲሆን የዲሲ መንግስት ቢሮ አካል በመሆኑ የቋንቋ ውስንነት ያለበት ማንኛውም ሰው አማርኛን ጨምሮ የቋንቋ አስተርጓሚ የመጠየቅ መብት አለው። ይህ ቢሮ ለተገልጋዮቹ ጊዜያዊ መፍትሄዎችን የሚሰጥ ሲሆን ከሌሎች ተቋማትጋ ትስስርን በመፍጠር ያግዛል። 

የማይግራንት ሶሊዳሪቲ ሙቹዋል ኤይድ በጎ ፈቃደኛ ይሆኑት ፊሸር “ማንም ሰው ላይ ፍርሀትን መጫር አንፈልግም። ግን ደሞ በእርግጠኝነት ይህ ማህበረሰብ በዚህ ወቅት ደህንነቱ የተጠበቀለትና ስጋት የሌለበት ማሀብረሰብ ነው ማለትም አንችልም” ያሉ ሲሆን። አክለውም “ይህ ሰው ስደተኛ ነው፤ ይህ ሰው ብዙ አልተጎዳም ብለን ሳንለይ በአንድነት ተባብረን ለእያንዳንዳችን ደህንነት መረባረብ አለብን።” ሲሎ አጠቃለዋል።  

ተጨማሪ የአማርኛ መረጃ በኢትዮጲክ ባልደረባ ከህግ ባለሞያዎችጋ በአማርኛ ያዘጋጀውን ዌቢናር መመልከት ይችላሉ።  

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *