ይህንን የሚያሳይ አውደ-ርዕይም ለዲሴምበር 8 1pm ተዘጋጅቷል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዝዳንት አንድሩ ፍሪድሰን፣ ፕሬዝዳንት ኬይት ስቱዋርት፣ የምክር ቤት አባላት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚው ማርክ ኤርልሪክ የማህበረሰብ አገልግሎት አቅራቢ እና ነዋሪዎች ”አገልግሎት በሕብረት ” United in Service” የሚል የማህበረሰብ ድጋፍ አውደ-ርዕይ እሁድ ዲሴምበር 8, 2024 ሮክቪል በሚገኘው የኤግዜክዩቲቭ ጽህፈት ቤት ሕንጻ ከቀኑ 1 ፒ ኤም እስከ 4 ፒ.ኤም አዘጋጅተዋል። ይህ አውደ ርዕይ በፌዴራል መንግስት ለውጥና በፖሊሲ ለውጦች ሊመጡ የሚችሉ ስጋቶችን በማሰብ ነዋሪዎች ሊኖሯቸው የሚገቡ የመረጃ አይነቶች በአግባቡ ይደርሳቸው ዘንድ የሚያረጋግጥ ሁኔታን የሚያመቻች ይሆናል።
ይህ ከክፍያ ነፃ የሆነ የማህበረሰብ መረጃ ማስጨበጫ መርሃግብር ነዋሪዎች ፈርጀ-ብዙ መረጃ ማለትም የማህበረሰብ ጤናና ደህንነት ፣ የሥነ-ተዋልዶ መብት፣ የሥራና የሙያ ሥልጠና አማራጮች፣ በአጠቃላይ ለነዋሪዎች መብታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ የሚቀርቡ አገልግሎቶችን የሚያሳውቅ መድረክ ይሆናል። ነዋሪዎች መብቶቻቸውን እንዲገነዘቡ የኮንትራት ፣ ሥራ ክህሎት ስልጠና እና የተለያዩ መረጃዎች ይቀርቡበታል።
”በዋሽንግተን ዲሲ የሚነገርም ሆነ የሚፈጠር ማንኛውም ሁኔታ ጥረታችንን የሚጋፋና የማህበረሰባችንን አገልግሎት የሚቀናቀን እንዲሆን ፈጽሞ አንፈቅድም ” ይላሉ የምክር ቤቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት አንድሩ ፍሪድሰን። ” ማህበረሰባችንን ከሚያግዙ ተቋማትና ከነዋሪው ጋር በጥምረት በመቆም ሞንትጎመሪ ካውንቲ እንደሁልጊዜውም ለመኖር የተመቸ፣ ነዋሪዎቹም ሠርተው ፣ በየእምነታቸው የታነፁ ቤተሰቦች አስተዳድረው የሚኖሩበት መሆኑን እናረጋግጣለን። ”
የካውንስል ፕሬዝዳንት ሆነው ባሳለፍነው ሳምንት የተሾሙት ኬይት ስቱዋርት በበኩላቸው እንደገለፁት ”በፌዴራል አስተዳደሩ በኩል አዲስ ለውጥ የሚጠበቅ ቢሆን የኛ ቀዳሚ ትኩረት የማህበረባችን ምቾት ሳይጓደል መቀጠሉ ላይ ነው” የኛ ኃላፊነት ነዋሪውን ለማገዝ ምን አገልግሎት እንደምናቀርብለት ማሳወቅና በማንኛውም ጊዜ እገዛ ሲፈልግ ከጎኑ መሆናችንን ማረጋገጥ ነው”። ብለዋል ኬይት ስቱዋርት ።
የካውንቲው ኤግዚኪዮቲቭ ማርክ ኤርልሪክ በበኩላቸው ” በፌዴራሉ አስተዳደር ምንም ዓይነት ለውጥ ቢመጣ የሞንትጎመሪ ነዋሪዎች ከበፊቱ አገልግሎት ምንም ሳይጎድልባቸው እንዲቀጥሉ በዚህ ዝግጅት ላይ የምናረጋግጥበት አጋጣሚ ይፈጠራል” ብለዋል።
“በህብረት መቆምና ነዋሪዎቻችንን ማገልገል የማያወላውል አቋማችን መሆኑን በዚህ ዝግጅት ለመግለጽ እንሻለን” ሲሉም የዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለዋል።
የአስፈጻሚው ቢሮ ህንፃ በሮክቪል 101 ሞንሮ ጎዳና ላይ ይገኛል። የማህበረሰብ የመርጃ ትርኢት በካፍቴሪያው ውስጥ ይካሄዳል።
ነፃ የመኪና ማቆሚያ በካውንስሉ ጽ/ቤት ህንፃ ጋራዥ በሞንሮ ጎዳና እና ፍሊት ጎዳና ወይም በምስራቅ ጀፈርሰን ጎዳና (መንገድ 28) እና ሞንሮ ጎዳና ጥግ ላይ በሚገኘው የዳኞች ማቆሚያ ቦታ ያለው ጋራዥ ይገኛል።
በሜትሮ ቀይ መስመር ላይ ያለው የሮክቪል ጣቢያ ለኮሚኒቲው የመርጃ ትርኢት በጣም ቅርብ የሆነ ማቆሚያ ነው።