Donald Trump

President-elect Donald Trump gestures after ringing the opening bell at the New York Stock Exchange, Thursday, Dec. 12, 2024, in New York. (AP Photo/Alex Brandon)

አሶሼትድ ፕሬስ፤ ዛሬ ሐሙስ ዲሴምበር 12 የኒው ዮርክ ስቶክ ኤክስቼንጅን ደወል ደውለው ያስጀመሩት ፕሬዘደንት ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ የአመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆነው በታይም መጽሄት ተሰይመዋል፡፡

President-elect Donald Trump arrives to ring the opening bell at the New York Stock Exchange, Thursday, Dec. 12, 2024, in New York. (AP Photo/Alex Brandon)

ፕሬዘደንቱ ደወሉን ከመደወላቸው በፊት “በታይም መጽሄት የአመቱ ሰው መባሌ ትልቅ ክብር ነው” ካሉ በኋላ ከመጀመሪያው ይልቅ ይህን ሁለተኛውን የተሻለ እንደወደዱት አክለዋል፡፡

ፕሬዘደንት ትራምፕ በባለቤታቸው ሜላንያ ትራምፕ፤ በሴት ልጆቻቸው ኢቫንካና ቲፋኒ እንዲሁም በምክትል ፕሬዘደንታቸው ጄዲ ቫንስ ታጅበውና በፈገግታ ደምቀው የነበረ ሲሆን በቦታው የነበሩ ታዳሚዎችም “”ዩ።ኤስ።ኤ”እያሉ ሲፎክሩላቸው ነበር፡፡

President-elect Donald Trump speaks during a Time magazine Person of the Year event at the New York Stock Exchange, Thursday, Dec. 12, 2024, in New York. (AP Photo/Alex Brandon)

የታይም መጽሄት ዋና አዘጋጅ ሳም ጄከብስ በኤን።ቢ።ሲ ቱዴይ ሾው ላይ የዘንድሮውን “የአመቱ ሰው” ማንነት ይፋ ሲያደርግ እንደተናገረው ትራምፕ ተወደደም ተጠላም በ2024 ዜናዎች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ነበራቸው ያለ ሲሆን አክሎም “እኚህ ሰው ታሪካዊ አመጣጥ ያላቸው ሲሆን በአሜሪካ ፖለቲካን ፕሬዘደንታዊ ስርዓት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡” ብሏል፡፡

ዜናውን ያገኘነው ከአሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.