
Credit: Fairfax County Park
በ2025 በካውንቲው ባሉ 10 ፋርመርስ ማርኬቶች ላይ ምርቶቻቸውን ይዘው መቅረብ የሚፈልጉ የምግብና ምግብ ነክ ምርቶችን የሚያመርቱ ነጋዴዎችን ማመልከቻቸውን መቀበል ሊጀምር እንደሆነ የፌርፋክስ ካውንቲ ፓርክ አስታወቀ፡፡ በማስታወቂያው ላይ እንደተገለጸው በፌርፋክስ ካውንቲ 125 ማይል ራዲየስ ውስጥ የሚገኙ ማናቸው የምግብ አምራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ ዲሲ ከፌርፋክስ ካውንቲ በ 20 ማይል ርቀት አካባቢ ላይ ይገኛል፡፡ ባልቲሞር በ 40 ማይል፤ ሪችመንድ በ100 ማይል አካባቢ ፤ ሀሪስበርግ ፔንሳልቬንያ በ110 ማይል አካባቢ እንዲሁም ፍሬድሪክስበርግ ቨርጂንያ በ50 ማይል ርቀት አካባቢ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ፋርመርስ ማርኬት ላይ ለመሳተፍ አመልካቾች ይዘውት የሚቀርቡትን የምግብ/መጠጥ አይነት ራሳቸው የሚያመርቱት መሆን አለበት፡፡ በዚሁ አካባቢ ካሉ ግብዐቶች ከተመረተ ደሞ ይበልጥ ተመራጭ ይሆናል ተብሏል፡፡

በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ ለሚፈልጉና ምርቶቻቸውን በፌርፋክስ ካውንቲ ባሉ 10 የፋርመር ማርኬቶች በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና የጥያቆእዎች መመለሻ ፕሮግራም ፓርኩ ለጃንዋሪ 14 አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ቨርቿል የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመሳተፍ ይህንን ተጭነው ይመዝገቡ፡፡ መረጃውን ያገኘነው ከካውንቲው ድረ ገጽ ነው፡፡