የዋሽንግተን ሪጅናል አልኮሆል ፕሮግራም (WRAP) ሁሌም እንደሚያደርገው የመጪው የገናና የአዲስ አመት በዓላትን በማስመልከትና ሰዎች ሰክረው እንዳያሽከረክሩ በማሰብ ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ላሉ ነዋሪዎች እስከ 15$ ድረስ የሊፍት ሂሳብ ይከፍላል።
ከ15 ብር በላይ ሂሳብ ከመጣ ከ15$ በላይ ያለውን ተሳፋሪዎች ራሳቸው መክፈል ይኖርባቸዋል። ድርጅቱ እስካሁን ድረስ በአስር ሰዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጥቷል። ይህ ፕሮግራም በዋናነት ለገናና አዲስ አመት፤ ለሴይንት ፓትሪክስ ቀን፤ ለ ሲንኮ-ዴ-ማዮ፤ ለኢንዲፔንደንስ ዴይ/ጁላይ 4ና ለ ኃሎዊን የነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል። በዚህ የነጻ ትራንስፖርት እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ መጠቀም ይችላሉ።
የሊፍት ኮዶቹ ዛሬ አርብ ዲሴምበር 13 ምሽት ከ 9፡00 pm ጀምሮ ይወጣል። ይህን ሊንክ ተከትለው በመሄድ የቅናሽ ኮዱን ማግኘት ይችላሉ። ኮዱ ለኡበር አይሰራም። ኮዱ ውስን ሲሆን ቀድመው ለመጡ ሰዎች ብቻ ነው የሚያገለግለው።