ከሰሞኑ ከየት እንደመጡ ያልታወቁ ድሮኖች በኒው ዮርክ፤ ኒው ጀርሲና ፔንሳልቫኒያ እንደታዩ በርካታ ሰዎች ጠቁመዋል። ከተራ ዜጎች በተጨማሪ ፖለቲከኞችና ባለስልጣናትም እነዚህን ጉዳዮች በተለያዩ መንገዶች ሲያወጡና ስጋታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። ከነዚህም አንዱ የኒው ጀርሲ 56ኛ ገቨርነር የሆኑት ገቨርነር ፊል መርፊ ለፕሬዘደንቱ ደብዳቤ እንዳስገቡና በደብዳቤው ስቴታቸው ያላቸው አቅም ውስን በመሆኑና ህጋዊ መብትም ስለሌለው የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብቶ ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲፈልግ እንደጠቀሱ አስታውቀዋል።
አክለውም በተመሳሳይ ለሲኤናተር ቸክ ሹመር፤ ለአፈ ጉባኤ ጆንሰን፤ ለሀውስ ሪፐብሊካን መሪ ሚች ማኮኔል እና ለ ለተወካይ ጄፍሪስ ለመሳሰሉ የህዝብ ተወካዮችም ደብዳቤ እንደላኩና በሴናተር ጌሪ ፒተርስና በሴናተር ሮን ጆን የቀረበውንና አገሪቱን ከድሮን ጥቃት እንዲከላከል ታስቦ የተዘጋጀውን የ2023 አዋጅ እንዲያጸድቁ ጠይቀዋል።
ትላንት ምሽት ዲሴምበር 12 ታዲያ በሂልስቦሮ ኒው ጀርሲ የወደቀ ድሮን አለ በሚል በርካታ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አካባቢው ዘግተው ሲፈልጉ የዋሉ ሲሆን ምንም አይነት ድሮን እንዳልተገኘ እንዲሁም ዛሬ አርብ ይህንን ወድቋል የተባለ ድሮን ለማግኘት በድሮን ፍለጋ እንደተካሄደ የአካባቢው ፖሊሶች አስታውቀዋል።
ዜናው ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰዎች በበርካታ አካባቢዎች ድሮን እንዳዩ እየጠቆሙ ሲሆን ከነዚ አንደ ደሞ የቀድሞ የሜሪላንድ ገቨርነር ላሪ ሆጋን አንዱ ናቸው። ገቨርነር ላሪ በትዊተር ገጻቸው እንዳጋሩት ራሳቸው በአይናቸው ድሮን እንዳዩና በቪዲዮ ቀርጸው እንዳስቀሩ የተናገሩ ሲሆን። መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግም አክለዋል።
ከኤፍ ቢ አይና ከዲ ኤች ኤስ በጋራ ያወጡት መግለጫ እንደሚለው ደሞ ታዩ የተባሉት ድሮኖች በአገርና በህዝብ ደህንነት ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለውና የውጭ ሀገራትጋም ግንኙነት እንዳለው ምንም ማስረጃ የለንም ብሏል።ከኒው ጀርሲ ፖሊስጋ በቅርበት በመሆንም ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነና የሰው ሀይልና የቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ በእርግጥም የታዩት ሰው አልባ ድሮኖች ይሁኑ አይሁኑ የማጣራት ስራ እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል።
ፕሬዘንደንት ትራምፕ በራሳውቸ ሶሻል ሚዲያ በትሩዝ ሶሻል ላይ ይህ ምስጢራዊ የድሮን በረራ ከመንግስት እውቅና ውጪ ሊሆን እንደማይችልና ጉዳዩ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ጠይቀዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ተኩሶ መጣልን እንደ አማራጭ አስቀምጠዋል።