አንባቢዎች በተደጋጋሚ በጠየቁን መሰረት የሜሪላንድ በተለይም የሞንጎምሪ ካውንቲ የአፎርደብል ቤቶች መረጃን ከሚያውቁ ጠይቀን ለመምጣት በማሰብ እንደመጀመሪያ እንዲሆነን ይህንን አጠናቅረናል።በሂደት ተጨማሪ መረጃዎችን እናመጣለን ለአሁኑ እዚህ ላይ ያሉትን ተጠቀሙባቸው።
የሞንጎምሪ ካውንቲ ሀውሲንግ ኦፖርቹኒቲ ኮሚሽን አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የካውንቲው ነዋሪዎች የቤት አቅርቦት ወይም ተያያዥ ጉዳዮች ድጋፍ ያደርጋል። ይህ ኮሚሽን ለደንበኞቹ በሁለት አይነት መንገድ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን አንዱ የሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ፕሮግራም ሲሆን ሌላኛው ደሞ የፕሮጀክት ቤዝድ ቫውቸር ነው። ሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር የቤት ኪራይ ድጋፉን በቀጥታ ለተከራዩ የሚሰጥ ሲሆን ተከራዩም በተፈቀደለት ገንዘብ ልክ የፈለገውን ቤት በካውንቲው ተከራይቶ መኖር ያስችለዋል። በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ የሚሆኑ ሰዎች ከገቢያቸው ከ40% በላይ ለቤት ኪራይ እንዳያውሉ ያግዛቸዋል።ገቢ ከሌላቸውም ሙሉ ኪራዩን ይሸፍንላቸዋል።
በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን የሚሹ ሰዎች ከገቢያቸው ሌላ የሚያስፈልጓቸው ዶክመንቶች ተብለው በተቋሙ ድረገጽ የተቀመጡት የሚከተሉት ናቸው
- Social Security numbers for all family members
- Signed release of information forms from all adults included in the application to participate in a mandatory criminal background investigation. NOTE: If the investigation reveals a criminal charge within the past three years, the Housing Choice Voucher application could be denied.
- Proof of U.S. Citizenship or a non-citizen with eligible immigration status. To prove eligible immigration status, you must have one of the following:
- Resident Alien Card
- Resident Alien Receipt Card
- Arrival/Departure Record
- Temporary Resident Card
- Employment Authorization Card
- Receipt issued by USCIS (U.S. Citizenship & Immigration Services) for the replacement of any of these items.
Every family member who is expecting to live in the household that is receiving Housing Choice Voucher assistance must have proof of eligibility (as stated above), with the following exceptions:
- If you are a “Mixed Family Household” then you are eligible for pro-rated (reduced) assistance. A “mixed family” is defined by HUD as “any family whose members include those with citizenship or eligible immigration status AND those without citizenship or eligible immigration”
- If your family includes both eligible and non-eligible members, then you will be considered a “mixed family”
በዚህ የ ሀውሲንግ ኦፖርቹኒቲ ኮሚሽን መልካም እድል ተጠቃሚ ለመሆንና ተመዝግበው ተራዎትን ለመጠበቅ ይህን ሊንክ ተጭነው በመሄድ መመዝገብ ይችላሉ።
በየጊዜው ካውንቲው ይፋ የሚያደርጋቸውን ክፍት የኪራይ ቤቶች ለማየት ደሞ ይህን ሊንክ በመጫን መረጃውን ማግኘት ይችላሉ። መልካም ዕድል!