የአሌክሳንድርያ ከተማ ለጃንዋሪ ክፍት የሆኑና ለከተማው አቅምን ያገናዘቡ የተባሉ የኪራይ ቤቶችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በዚህ ዝርዝር ላይ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች የሚገኙ ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለ አንድ፤ ባለ ሁለትና ባለ ሶስት መኝታ መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር የተካተቱ ሲሆን እድሚያቸው ከ62 በላይ ለሆኑ አዛውንቶችን ጨምሮ ለማንኛውም ሰው የሚሆኑ ቤቶች እንዳሉ ተጠቁሟል።
ከነዚህ ቤቶች አከራዮች የተወሰኑት (እንደ “ዘ ስፓየር” ያሉት) ተከራዮችን ለማማለል የመጀምሪያ ወር የቤት ኪራይን ነጻ እንዳደረጉ ጭምር መግለጫው ላይ ተካቷል።
ገቢን ያገናዘቡ (አፎርደብል ቤቶችን) ለመከራየት ከዚህ ቀደም የነበረው የገቢ መጠን ከጃንዋሪ 2025 ጀምሮ የተስተካከለ ሲሆን አዲሱ የገቢ መጠን እንደሚከተለው ሰንጠረዥ እንደሚሆንም መረጃው ያመለክታል።
የነዚህን ቤቶች ሙሉ ዝርዝር ለማየትና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ።