12/12/2024

ከ2021 ጀምሮ በethiopique.com ድረ-ገፅ ላይ በርካታ አገልግሎትን በበጎ ፈቃደኝነት ያበረከተችው የቪኦኤ ጋዜጠኛዋ ኤደን ገረመው ሞንትጎመሪ ሴቶች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሴቶች የ2022 የሴት ታሪክ ሰሪዎች ሽልማት ኮሚቴ በሚያዘጋጀው የእውቅና ፕሮግራም ላይ አንዷ ታሪክ ሰሪ ተብላ ተመርጣለች።


የሞንጎምሪ ካውንቲ ስራ አስፈፃሚ ማርክ ኤልሪሽ ይህን ሽልማት ለተቀበሉት 31 ምርጥ ሴቶች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም አሸናፊዎች ለማህበረሰባቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ እና ለሌሎች ባበረከቱት ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ነው። የሞንጎምሪ ካውንቲ ስራ አስፈፃሚ ማርክ ኤልሪሽ አክለውም “ሁሉም ተሸላሚዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል፤ ልዩ የአመራር ብቃት በማሳየት፣ ሌሎች ነዋሪዎችንም በማነቃቃት እያገለገሉ ይገኛሉ።

እነዚህን ታሪክ የሰሩ ሴቶች እየዘከርን በቀጣይ ደግሞ ተተኪ ሴት መሪዎችን ለማብቃት እንቅስቃሴያችን መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። የሁሉንም አሸናፊዎች ዝርዝርና ሙሉ መግለጫውን ይህን ሊንክ ተጭነው ማግኘት ይችላሉ።

ይህ የሽልማት ፕሮግራም በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለሙያቸው እና በማህበረሰባችን ውስጥ ጉልህ አስተዋፅኦ ላደረጉ ሴቶች እውቅና ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።


ኤደንን ጨምሮ የዚህ ታሪካዊ ሽልማት የተመረጡ ሴቶች በተከታዩቹ መስፈርቶች ተመዝነው በአንዱ አሊያም ከዚያ በላይ በሆኑት ብቁ ሆነው እንደተገኙ የሽልማቱ አዘጋጆች ገልፀዋል

  • ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ አመራር እና በተሰማሩበት ዘርፍ ጠንክሮ መሥራት
  • በሲቪክ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ልዩ አመራር ማስመዝገብ
  • አዎንታዊ ማህበራዊ እርምጃ የሚያስከትሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ወይም መደገፍ
  • ለሌሎች መነሳሳት በአርአያነት ያገለገሉ

ቲም-ኢትዮጲክም በተዘዋዋሪ የዚህ ሽልማት አካል በመሆናችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል። ለኤደን ገረመውም እንኳን ደስ ያለሽ እንላለን። ደስታሽ ደስታችን ነው!!

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት