የካርሎስ ሮዛሪዮ ትምህርት ቤት በዲሲ-ሜትሮ አካባቢ ለሚኖሩ አዋቂዎች በቋንቋና በተለያዩ የክህሎት ዘርፎች ስልጠናዎችን በተመጣጣኝ ክፍያና በነፃ የሚያቀርብ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት እንግሊዝኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ መማር ለሚፈልጉና በዲሲ ሜትሮ ለሚኖሩ አዋቂዎች የቋንቋ ትምህርት ይሰጣል። በዚህ የቋንቋ ትምህርት ተሳታፊ ለሆኑ ተማሪዎቹና ለሌሎችም ነዋሪዎች ደግሞ እንደ ረዳት ነርስ፤ ኮንስትራክሽን፤ ረዳት የክፍል መምህርነት፤ የምግብ ስራ ሙያ፤ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በነፃ የሚያሰለጥን ሲሆን ስልጠናዎቹን ሙሉ ለሙሉ ላጠናቀቁ ተማሪዎች ስራ ለመያዝ የሚያግዛቸውን ድጋፍ ያደርጋል።
ትምህርት ቤቱ የአማርኛ መምህራንና አስተርጓሚዎች ያሉት በመሆኑ የቋንቋ አለመግባባት እንዳይፈጠርና ብዙ ኢትዮጵያውያን ድርጅቱ በሚያዘጋጃቸው መልካም እድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ረድቷል።
በዚህ እድል መጠቀም ከፈለጉ ይህን ሊንክ ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ።
ስለ ካርሎስ ሮዛሪዮ የበለጠ ለማወቅ ይህን ሊንክ ተጭነው ማየት ይችላሉ።