12/12/2024

ሞንጎምሪ ካውንቲ መዝናኛ ለበጋ/ሰመር/ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰራተኞችን ለመመልመል ማስታወቂያ አውጥቷል። ካውንቲው በድረ-ገፁ እንዳስቀመጠው አስቀድመው የስራ ኢንተርቪው የያዙ አመልካቾችን ቅዳሜ ኤፕሪል 9፣ 2022 ኢንተርቪው ለማድረግ ማቀዱንና ፍላጎቱና ችሎታው ያላቸው ሰዎች አስቀድመው ቀጠሮ እንዲይዙ አስታውቋል። ካውንቲው የስራ ቅጥር ኢንተርቪው አደርግባቸዋለሁ ካላቸው የስራ ዘርፎች የውሃ ዋና፤ የአዛውንቶች የመዝናኛ ቦታ ጠቅላላ አገልግሎት፤ የበጋ ካምፕ/ሰመር ካምፕ/፤ አፍተር ስኩል ፕሮግራምና የወጣቶች ስራ ይገኙበታል። በወጣቶች የስራ ዘርፍ እድሜያቸው ከ 14-21 ለሆናቸው ታዳጊዎችና ወጣቶች ለወደፊት ህይወታቸው የሚያዘጋጇቸው ስራዎች ተዘጋጅተዋል።

በነዚህ የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ከፈለጉና ለኢንተርቪው ቀጠሮ ማስያዝ ከፈለጉ ወይንም የበለጠ መረጃ ካሻዎ ይህን ሊንክ ተከትለው ይሂዱ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት