12/12/2024
Screen-Shot-2022-04-04-at-14.57.50

የሞንጎምሪ ካውንቲ የጊልክሪስት የስደተኞች ድጋፍ ማዕከል መኖሪያቸውን በሜሪላንድ ሞንጎምሪ ካውንቲ ላደረጉ ስደተኞች የኦንላየን የእንግሊዝኛ የቋንቋ ስልጠና ምዝገባ ጀምሯል።
የጊልክሪስት ማዕከል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸውና የእንግሊዝኛ ክህሎታቸውን ማዳበር የሚሹ የካውንቲው ነዋሪዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል። ያለው ቦታ ውስን በመሆኑ ቅድሚያ ለሚመዘገቡ ነዋሪዎች ብቻ ስልጠና እንደሚሰጥ የፕሮግራሙ አዘጋጆች አስታውቀዋል። ምዝገባው ከኤፕሪል 4 ጀምሮ የመማሪያ ክፍሎቹ እስኪሞሉ ክፍት ይሆናል።

ስልጠናው ዘወትር ከሰኞ-ዓርብ ምሽት ላይ አልያም ቅዳሜ ግማሽ ቀን እንደምርጫዎ ይሰጣል።
ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት