ለልጆችዎ የገዟቸውና አሁን አገልግሎት የማይሰጡ የቡስተር ሲት በቤታችሁ ያሏችሁ ወላጆች ከትላንት ኤፕሪል 18 ጀምሮ እስከ ኤፕሪል 30፣ 2022 በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ታርጌት በመውሰድ በቅያሪው የ20% ቅናሽ ኩፖኖች መውሰድ ይችላሉ። በነዚህ የቅናሽ ኩፖኖች የልጆች ስትሮለር፤ ሌላ የመኪና መቀመጫ፤ ወይንም ሊሎች የህፃናት ፈርኒቸሮች መገብየት ይችላሉ።
በተጨማሪም በዘንድሮው ፕሮግራም ተሳታፊ ሲሆኑ ኩፖንዎን ሁለት ጊዜ (ለ2 ግብይት 20% ቅናሽ) መጠቀም ይችላሉ።